አማኑኤል አማን

አማኑኤል

ደራሲና ጋዜጠኛ አማኑኤል አማን(ታደሰ ከበደ በላይ) ከ25 ዓመታት በላይ በግሉ ፕሬስ የተለያዩ መፅሔቶችና ጋዜጦች ዋና አዘጋጅ በመሆን ያገለገለ ሲሆን ከ2007 ዓመት በኋላ ደግሞ የሙሉ ጊዜ ፅሐፊ በመሆን ሰባት መፅሐፍትን ለሕትመት በማብቃት ከፍተኛ ተነባቢነትን በማትረፍ በስነፅሑፉ ዕድገት ላይ የራሱን አሻራ ያሳረፈ ደራሲ ነው። በተለይም "የኃያላኑ ሴራ በኢትዮጵያ" የሚለው ሁለተኛው መፅሐፉ ከመቶ ሽህ ኮፒ በላይ የተሸጠ ሲሆን አሁንም ድረስ ሕትመቱ ሳይቋረጥ በመቀጠል ላይ ይገኛል። ደራሲው በዚህ መፅሐፉ "መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች።" የሚለውን የመዝሙረ ዳዊት ትንቢት በመተንተን :- ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በቃልኪዳን መፅሔት፣ በቃል አምባ መፅሔትና በአዲስ ጊዜ መፅሔት እንዲሁም በ2009 ዓ.ም ለንባብ ባበቃው "የኃያላኑ ሴራ በኢትዮጵያ" በሚለው መፅሐፍ :- ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት እንደምትሰነዝር፣ የዓለም ኃያላንም ከግብፅ ጎን ተስልፈው በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያደርጉ በመተንበይ መንግስትና ሕዝብን ሲያሳስብና ሲያስጠነቅቅ ቆይቷል። ደራሲው በሰባቱም መፅሐፍቱ :- ኢትዮጵያዊያን ከወደቀባቸው የመደንዘዝ አዚም ተላቀው የጠላትን እኩይ ሴራ በአንድነትና በዓላማ ፅናት እንዲታገሉ፣ የኢትዮጵያዊነት እሴቶችን እንዲያስቀጥሉና በግለሰብ ደረጃ በሁሉም ማዕዘን የአስተሳሰሰብ ለውጥ እንዲያመጡ ሰፊ ጥረት አድርጓል። በአሁኑ ወቅትም አምስቱ መፅሐፍቶቹ በAfroRead መተግበሪያ ላይ ይገኛሉ።

Books by አማኑኤል:

የገሃነም ደጆች ፖለቲካ

የገሃነም ደጆች ፖለቲካ

Fiction, Politics, Literature, Sociology

የአዲስ አበባ ድብቅ ገመናዎች

የአዲስ አበባ ድብቅ ገመናዎች

Fiction, Literature, Addis Ababa City Life

የአዲስ አበባ ድብቅ ገመናዎች

የአዲስ አበባ ድብቅ ገመናዎች

Fiction, Addis Ababa City life, Literature, Sociology

የሳጥናኤል ፊታውራሪዎች

የሳጥናኤል ፊታውራሪዎች

Fiction, Politics, Literature, Sociology