የአዲስ አበባ ድብቅ ገመናዎች

የአዲስ አበባ ድብቅ ገመናዎች

Author/s: አማኑኤል አማን

Subjects

Fiction, Literature, Addis Ababa City Life

Published Year

2012 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

የአዲስ አበባ ድብቅ ገመናዎች የተሰኘው የደራሲ አማኑኤል አማን መፅሐፍ ከሌሎቹ ስራዎቹ ለየት ያለ አቀራረብና ቅርፅ ይዞ የመጣ ነው። በቋንቋ ውበት የበለፀገ፣ አዝናኝና አስደማሚ የወግ መፅሐፍ ነው። በዚህ መፅሐፍ ቁመተ ረጃጅምና ወርደ ሰፋፊ የወሲብ አማልክት የሚራኮቱበት የሰባተኛ ዝሙት አዳሪነት፣ እንደ እንዝርት ሹረው የሚያሾሩ ቁጡና ቅብጥብጥ እመቤቶች ገመና፣ በ300 እና 400 ካፒታል ብር መርካቶን ስለሚዘውሯት የምናለሽ ተራ ኢንቬስተሮች፣ ገንዘብ ሳይኖራቸው የሚገዙ-ያልገዙትንም የሚሸጡ ምትሀተኛ ቃፊሮች፣ የእሪ በከንቱ የጨለማ ትርዒቶች፣ የባሻ ወልዴ ችሎት የረብሻ ትርምስምስታ፣ የኮልፌ የጭርታ ደፈጣ፣ የካዛንችስ የማስመሰል ፊንታ ...እንዲሁም የሌሎች የአዲስ አበባ እህትማማች ሰፈሮች አኗኗርና ውስጠ-ምስጢር በጊዜያቸው የነበራቸው ሁኔታ በስፋትና በጥልቀት ተዳሰዋል። በእርግጠኝነት እያለቀስን የምንስቅባቸው ፣ እየተዝናናንም የመጣንበትን አስቸጋሪና ጠመዝማዛ መንገድ የምንመለከትባቸው ትዕይንቶች በእዚህ መፅሐፍ ተካተዋል ።

5.0 (1 reviews)