ሲሳይ ንጉሡ

ሲሳይ

ሲሳይ ንጉሡ በ1951 ዓ.ም አዲስ አበባ ተወለደ:: በውጪ ቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአሥመራ ዩኒቨርስቲ የወሰደ ሲሆን፣ በትምህርት አስተዳደርና አመራር የማስተርስ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝቷል፡፡ የሥነ-ጽሁፍ ፍላጎት ያደረበት ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ #ጉዞው$ የተሰኘው ኖቬላ የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ የፃፈውና የህትመት ብርሀን ያየው የመጀመሪያ መፅሐፉ ነው፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሆኖ የፃፈውና ያሳተመው #ሰመመን$ የተሰኘው ልቦለድ የፍቅር መፅሐፍ ዝናን አትርፎለት ከሰፊው አንባቢ ጋር ለመተዋወቅ በቃ፡፡ ከዚያ በኋላም ሙሉ ጊዜውን ለድርሰት ሥራ በመስጠት ግርዶሽ፣ ትንሳኤ፣ የቅናት ዛር እና ረቂቅ አሻራ የተሰኙ ረዥም ልቦለዶችን አሳትሟል፡፡ አጫጭር ልቦለዶችንም በተለያዩ መፅሔቶች ላይ አቅርቧል፡፡ በስነ-ፅሁፍ ሥራው በርካታ ሽልማቶች ተበርክተውለታል፡፡ ሲሳይ ንጉሡ ባለትዳርና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነው፡፡

Books by ሲሳይ:

ሰመመን

ሰመመን

Fiction, Literature

ረቂቅ አሻራ

ረቂቅ አሻራ

Literature, Fiction

ግርዶሽ

ግርዶሽ

Literature, Fiction

ሰመመን

ሰመመን

fiction, literature