ሰመመን

ሰመመን

Author/s: ሲሳይ ንጉሡ

Subjects

fiction, literature

Published Year

በ1978 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

ሰመመን የሁለት ወጣቶች የአይን ፍቅር ታሪክ ነው ። አፍቃሪና ተፈቃሪ ተቀራርበው ሳይነጋገሩ እንዲያው በአይን ፍቅር ብቻ እየተሰቃዩ ይቆያል ። መቼቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲሆን ገፀባህርያቱ ደግሞ ተማሪዎች ናቸው ። አቤል ጎበዝ ተማሪ ነበር ። ነገር ግን በአይን ፍቅር ከታወረ ጀምሮ በትምህርቱ እየደከመ ይሄዳል ። ተፈቃሪዋ ትእግስት ችግሩን ብትረዳለትም እሷም አይንአፋር በመሆኗ ልትረዳው ወይም ቀርባ ልታነጋግረው አልቻለችም ። ሁለቱም በየፊናቸው ይሰቃያሉ ። ጓደኞቻቸውም ለመርዳት ይቸገራሉ መምህር ዮናታን ጎበዝ ተማሪያቸውን ለማዳን ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ ።ታሪኩ የሁለቱ ወጣቶች የአይን ፍቅር ይሁን እንጂ የዩንቨርስቲን ህይወት በስእላዊ መልክ የሚያሳይ ነው ። ተዋንያኑ ተማሪዎች ናቸው ። ከድብርታሙ እስከ ቀልደኛው ከደካማው እስከ ጉልበተኛው ከግዴለሹ እስከ አስተዋዩ ሁሉም በየፈርጁ ተስሏል ። የፈተና ሰሞን ድባብ በገና ማዕበል ተመስሎ ቀርቧል ። የካምፓስ ቀልዶች ከቁም ነገር ጋር እየተደበላለቁ በየምዕራፉ ያዝናናሉ ።ታሪኩ ልብ ይሰቅላል ። አንባቢ በሳቅና ቁምነገር እየተዋዛ የሁለቱን የአይን ፈቅረኞች መጨረሻ ለማየት አብሮ ይጓዛል ።

0.0 (0 reviews)