ሰመመን

ሰመመን

Author/s: ሲሳይ ንጉሡ

Subjects

Fiction, Literature

Published Year

በ1978 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ሰመመን የሁለት ወጣቶች የዓይን ፍቅር ታሪክ ነው፡፡ አፍቃሪና ተፈቃሪ ተቀራርበው ሳይነጋገሩ እንደዲያው በዓይን ፍቅር ብቻ እየተሰቃዩ ይቆያሉ፡፡ መቼቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሲሆን ገፀባህርያቱ ደግሞ ተማሪዎች ናቸው፡፡ አቤል ጎበዝ ተማሪ ነበር፡፡ ነገር ግን በዓይን ፍቅር ከታወረ ጀምሮ በትምህርቱ እየደከመ ይሄዳል፡፡ ተፈቃሪዋ ትዕግስት ችግሩን ብትረዳለትም እሷም አይንአፋር በመሆኗ ልትረዳው ወይም ቀርባ ልታነጋግረው አልቻለችም፡፡ ሁለቱም በየፊናቸው ይሰቃያሉ፡፡ ጓደኞቻቸውም ለመርዳት ይቸገራሉ፡፡ መምህር ዮናታን ጎበዝ ተማሪያቸውን ለማዳን ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ታሪኩ የሁለቱ ወጣቶች የዓይን ፍቅር ይሁን እንጂ፣ የዩኒቨርስቲን ህይወት በሥዕላዊ መልክ የሚያሳየይ ነው፡፡ ተዋንያኑ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ከድብርታሙ እስከ ቀልደኛው፣ ከደካማው እስከ ጉልበተኛው፣ ከግዴለሹ እስከ አስተዋዩ ሁሉም በየፈርጁ ተስሏል፡፡ የፈተና ሳሞን ድባብ በገና ማዕበል ተመስሎ ቀርቧል፡፡ የካምፓስ ቀልዶች ከቁም ነገር ጋር እየተደባለቁ በየምዕራፉ ያዝናናሉ፡፡ ታሪኩ ልብ ይሰቅላል፡፡ አንባቢ በሳቅና ቁምነገር እየተዋዛ የሁለቱን የዓይን ፍቅረኞች መጨረሻ ለማየት አብሮ ይጓዛል፡፡

0.0 (0 reviews)