ረቂቅ አሻራ
Summary
ረቂቅ አሻራ በሀገራችን የሰፈነውን የሞራል ውድቀት ለመታደግ የተፀነሰ ልብ ወለድ መፅሐፍ ነው፡፡ ዋናው ገፀ-ባህርይ አጥናፍሰገድ የሀብቱ ምንጭ የሜሪኩሪ ቅብብሎሽ በመሆኑ "የሜሪኩሪ ጌታ" በሚል ቅፅል ስም ይታወቃል፡፡ በቁንጅና ውድድር አሸንፉ ወይዘሪት ኢትዮጵያ የተባለቸውን ሴት ያፈቅራል፡፡ ህሊና ታደሰ ትባላለች፡፡ አድናቂዎቹ የሞራል ዕመቤት ይሏታል፡፡ አጥናፍሰገድ ቢመኛትም ህሊና በቀላሉ የምትገኝ አልሆነችም፡፡ በደላላ ሊያገኛት ይሞክራል፤ በምኞት ይሰቃያል፡፡ ህሊናም ፈተናውን ታበዛበታለች፡፡ ከራሱ ህሊና ጋር ካልታረቀና መንፈሱን ካላፀዳ እሷን ማግኘት አይችልም፡፡ በመፅሐፉ ውስጥ ከትንሽ እስከ ትልቅ ሁሉም በሜርኩሪ ዙሪያ ይፋለማሉ፡፡ ወንጀሎች ይፈፀማሉ፣ ወንጀለኞች ይተናነቃሉ፡፡ ብዙዎቹ በምኞት ይሰክራሉ፡፡ ህሊና በተምሳሌትነት የቀረበች የእያንዳንዳችን ህሊና ምስል ናት፡፡ ሥጋዊ ምቾት በዝቶ መንፈሳዊ ዕጦት ሲመጣ፣ ዕመነት ሲረክስ፣ ፍቅር ሲጠፋና መጠላለፍ ሲበዛ የሞራል ውድቀት ይከተላል፡፡ ንቅዘት ይበዛል፡፡ ሙስና ይስፋፋል፡፡ ህሊና እነዚህን ጥፋቶች ለመታደግ የሞራል ኮሌጅ እስከ መክፈት ትደርሳለች፡፡ ጥረቷ ሰምሮላት የጠፉትን ሁሉ መመለስ ትችል ይሆን? አጥናፍሰገድስ በፀበሏ ተጠምቆ ወደ ህሊናው መለስ ይችል ይሆን?