ሄኖክ ግርማ

ሄኖክ

ሄኖክ ግርማ የተወለደው አዲስ አበባ ነው፡፡ ወደ ደራሲነት ህይወት ሙሉ በሙሉ የገባው ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ቢሆንም ከዚያ በፊት በነበረው የትኛውም ጊዜው ኪነጥበቡን እርቆ የማያውቅ ሰው ነው፡፡ በመሆኑም በተለያዩ ጊዜያት ከሶስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ጊዜን የወሰዱ የጋዜጠኝነት፣የስነፁሁፍ፣የፊልም ስራ ጥበብ፣የስነ ሥዕል ሙያ ስልጠናዎችን የወሰደ ሲሆን ከዚያ ባለፈም ከኪነ ጥበቡ ዓለም ውጪ ባሉ ሌሎች ሙያዎች ስልጠናዎችን ወስዷል፡፡ ከዚያ መካከልም በኢትዮጲያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሚተዳደረው ቀደምት የሆቴልና የቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት (ctti) ተምሮ ተመርቋል፡፡ ወደ ድርሰቱ ዓለም ከገባ በኋላም ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የታተሙና ያልታተሙ የልቦለድ፣የግጥም፣የወግ፣የእውነተኛ ታሪኮች፣ የህፃናት እንዲሁም የትምህርት ስልጠና መፃህፍት አዘጋጅቷል፡፡