የጎዳናው እውነት

የጎዳናው እውነት

Author/s: ሄኖክ ግርማ

Subjects

Fiction, Literature, History

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

በመሃከላቸዉ ጸጥታ ሰፍኗል ፡፡የአምስቱም ልጆች አይኖች አንድ አቅጣጫ ላይ አተኩረዋል ፡፡አይኖቼ የእነሱን አይኖች ተከትለዉ ከተቀመጥኩበት ቦታ በስተቀኝ ወደ አለዉ የመንገዱ ክፍል ተወረወሩ፡፡ ሁለት ሴት የጎዳና ተወዳዳሪዎች አንዲት ጓደኛቸዉ ከኋላቸዉ ሱክ ሱክ እያለች ትራመዳለች ፡፡ ሴቶቹ እኔ ወዳለሁበት እየተቃረቡ ሲመጡ አተኮርኩባቸዉ ፡፡እንደ ወንዶቹ ጎዳና ተወዳዳሪዎች ሁሉ ሴቶቹም ቀን ላይ እዚያዉ አካባቢ የሚዉሉና በአይን የማዉቃቸዉ ናቸዉ፡፡በተለይ ደግሞ መሃከል ላይ ሆና በሁለት ጓደኞቿ ተደግፋ የምትሄደዉጥረ ቢጫ ሆኖ ተንንሽ አበባ ከየቦታዉ የተሳለበት ስስ ጉርድ ቀሚስ ከሰዉነቷ ጋር ጥብቅ ካለ ካናቴራ ጋር የለበሰችዉን ልጅ ሳዉቃት ሶስት አራት አመት ይሆናል ፡፡ ልጅቷን ለመጀመርያ ጊዜ ሳያት አስር አመት ቢሆናት ነበር፡፡በጣም ትንሽ ቆንጆ ደስ የምትል ህጻን ልጅ ነበረች በዚያን ጊዜ ፡፡ይህች ልጅ ጎዳና ላይ መታየት ከጀመረች ሁለት አመት ያህል እንዳለፈ ግን አንዱ የፊት ጥርሷ ወልቋል ፡፡የጎዳናዉ ኑሮ አለመመቸት ከጥርሷ መዉለቅ ጋር ተደርቦ ልጅቷ ሌላ ሰዉ ስትመልስ ጊዜ አልፈጀባትም ፡፡ በዚያ ሁኔታ ላይ እያለችም ሰዉነቷ በመጠኑከፍ ብሎ ተለቅ ያለ ሎሚ የሚያክል ጡት ደረቷ ላይ በቅሎ ሰዉነቷ የታዳጊ ኮረዳዎችን ቅርጽ ለመያዝ ሞካክረዉ ፡፡ ይሄኔ ነዉ እንግዲህ በሁለት ጓደኞቿ ተደግፋ እያነባችና ትዉከቷን መንገድ ለመንገድ እየዘረገፈች ተቀምጬ ወደነበረበት ቦታ ስትመጣ ለማየት የበቃሁት ፡፡

0.0 (0 reviews)