ስልክሽን ልያዘው
Summary
እሷና ሰውየው ጉንጮቻቸውን እያነካኩ ተሳስመው ሲያበቁ ለእኔም እጆቿ ደረሱኝ፡፡ መዳፏ በጣም ይለሰልሳል፤ልስላሴው ደግሞ እኔን በቅፅበት ዓመታት ወደኋላ እንድመለስ አደረገኝ፡፡ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ያፈቀርኳት እፀገነትን ለመጀመሪያ ጊዜ ስጨብጣት የእባብ ቆዳ የነካሁ ነበር የመሰለኝ፡፡ ‹‹ዕጅሽ ይለሰልሳል›› ብያትም ነበር የዩኒፎርሜን እጅጌ እየቆለፍኩ፡፡ ‹‹ያንተ ስለሚሻክር ይሆናል›› አለችኝ ለሞራሌ እንኳን ሳትጠነቀቅ፡፡ ዛሬ ደግሞ ከጊዜያት በኋላ ቡና ቤት ውስጥ ፀጊን የሚፎካከር የዕጅ ልስላሴ ያላት ልጅ ገጠመችኝ፡፡