የፍቅር ሀሁ እና ሌሎች

የፍቅር ሀሁ እና ሌሎች

Author/s: ሄኖክ ግርማ

Subjects

Fiction, Literature

Published Year

2008 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

በዚያን ወቅት እኔ ከስራ ስወጣ እሷን ካላገኘሁ ያመኛል ደሞዜን ለእሷ ካላካፈልኩኝ ገንዘቧን የሰረኳት ይመስለኛል፡፡ያለችኝን ካላደረኩኝ በእሷ ላይ ያደምኩኝ በእሷ ላይ ጦርነት ያወጅኩኝ ሆኖ ይታሰበኛል የእሷን ምክርና አስተያየት ካልተቀበልኩኝም ይጨንቀኛል፡፡በጊዜዉ በሆዴ የሚቀመጥ የግሌ የሆነ ሚስጥር እንኳን አልነበረኝም፡፡ምክንያቱም የሚስጥሬ ካዝና እሷ ነበረች ክብደቴን መመዘንም ሳይቀር አቁሜ ነበር ምክንያቱም የክብደቱም ሆነ የሁለመናዪ መጨመር መቀነስ መግዘፍና መኮሰስ የሚነገረኘ አይሳሳትም ብየ ባመንኩበት የእሷ አንደበት ሆኖ ነበር፡፡ የፍቅር ሀሁ እንደዛሬዉ አስተሳሰቡ ከሆነ እነሱ ንቀት የሚገባቸዉ ናቸዉ፡፡ምክንያቱም እነሱ ሲያገለግላቸዉ የኖረዉን እሱን ንቀዉታል ፡፡እነሱ በእሱ እየተገለገሉ ጥቅሙን አሳንሰዉ ከናቁት እሱ በቀጥታ የማያገለግሉት እነሱን ቢንቃቸዉ የሚገባ ነዉ፡፡ስለዚህም ቤቱ ዉስጥ ተቀምጦ የሚሉትን እንዳልሰማ በመሆን ዝም ብሏቸዋል፡፡ ዉሃ አስቀጅዉ ሃሳባችን ተሳክቶ ተጋብተን ልጆች ከወለድን በኋላ ልጆቻችን አድገዉ እኔና ባለቤቴ የትና እንዴት እንደተገናኘን ከጠየቁም ‹‹እኔ ወረቀቶች በእጄ ይዤ ወደ ቤተ መጽሃፍት ስሄድ እናታችሁን ጠብመንጃ ይዛ ቤተመጽሃፍት አካባቢ አገኘኋት ወደ እሷ ተጠግቼም … ስጦታ ‹‹እ ምንድነዉ አንጀቴ››አሏት አሮጊቷ በእድሜ ብዛትና በኑሮ ጉዳት የዛለ ሰዉነታቸዉን ከተኛበት ለማንሳት እየጎተቱ ‹‹እርቦኛል እማ ››ብላ የለቅሶ ዜማ ባለዉ ድምጽ አላዘነች ‹‹እ›› ኑኑሽ ይህች ለሰዉ አዛኝ የሆነችና ‹‹ጠላትህን ዉድድ››የሚለዉን ቃል የህይወት መመርያዋ አድርጋ ለመንቀሳቀስ የምትሞክር ዘመዴ ታድያ ጠንካራ የጉልበት ሰራተኛ ነች፡፡ለወደፊት መንጃ ፍቃድ አዉጥታ በሹፍርና ስራ ስራ ላይ ለመሰማራት እቅድ ያላት ቢሆንም አሁን ግን እየሰራች ያለችዉን የአትክተኛነት ስራ በትጋት እየሰራች ነዉ የምትገኘዉ፡፡ ሽፍንፍን ሽንፈት

3.0 (1 reviews)