ህይወት ተፈራ
ሕይወት ተፈራ ተወልዳ ያደገችው በምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል በሐረር ከተማ ነው ፡፡ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በሐረር ከተማ ከተከታተለች በኋላ ወደ አዲስ አበባ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተዛወረች፡፡ ሁለተኛ ዲግሪዬን በአንትሮፖሎጂ/ሶሺሎጂ አጠናቃለች፡፡ ለህትመት መጀመርያ የበቃው የስነ ፅሁፍ ስራዋ እ.ኤ.አ. በ 2012 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የታተመው "Tower in the sky" የተሰኘው መጽሐፍ ነው ፡፡ መጽሐፉ በ 1960 ዎቹ መጨረሻ እና በ 70 ዎቹ መጀመሪያ ላይ በተማሪዎች አብዮት ውስጥ ስለተሳተፈችበት እና በኢሕአፓ ፓርቲ ውስጥ የነበራትን ሚናና የፍቅር ሂወት የሚዳስስ ነው ፡፡ "Mine to Win" እና "ምንትዋብ" የተሰኙት ሁለት መጽሐፍት ደግሞ በመቀጠል ለህትመት የበቁ የደራሲዋ የስነ ፅሁፍ ስራዎች ናቸው ። "Tower in the sky" እና "Mine to Win" ሁለቱም ወደ አማርኛ ተተርጉመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሕይወት ተፈራ ከ28 አመት የካናዳ ኑሮ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየኖረች ትገኛለች ፡፡