ሰለሞን ሳህለ

ሰለሞን

ሰለሞን ሳህለ እባላለሁ ወጣት ፀሀፊ ነኝ፡፡ ከመጀመርያ ትምህርት አንስቶ አሁን እስካለሁበት ጊዜ ድረስ የጥበብ ቤተሰብ ሆኜ ነው ያደኩት፡፡ ከሚኒ ሚዲያ ጀምሮ የተነሳው የስነ-ፅሁፍ ፍላጎቴና ችሎታዬ በሀገሪቱ አሉ እስከተባሉ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ በአዘጋጅነት እና በፅሀፊነት እንድሰራ አድርጎኛል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋ እና ሥነ-ፅሁፍ ተምሬያለሁ፡፡ በተለያዩ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ላይ በርካታ የጥበብ ስራዎቼ ተነበውልኛል፡፡ በተለያዩ የስነ-ጽሁፍ የውድድር መድረኮች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ አሸናፊ ሆኔ ተሸለሚያለሁ፡፡ ከ6 በላይ የመጽሃፍ ስራዎቼ በጋራና በግል ታትመው ለህዝቡ ተነባቢ ሆነውልኛል፡፡ 1. የፍቅር እንባዎች (አጫጭር ልብወለዶች) በጋራ 2. ያማል (የግጥም መድብል) በግል 3. የልብ ማህተም (የግጥም መድብል) በግል 4. በመሰንቅ (የግጥም መድብል) በግል 5. ሰምናወርቅ (የግጥም መድብል) በጋራ 6. አላፍ ታሪክ (አጫጭር ልብወለዶች) በጋራ ...ስራዎቼ ተወዳጅነትን በማትረፋቸው ለ5 ጊዜ ያክል ለህትመት በቅተዋል፡፡ አሁንም ተነባቢ ናቸው፡፡ለወደፊቱም ለህትመት የተዘጋጁ በርካታ ስራዎቼ ጊዜያቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡በአሁኑ ሰዓትም የሙሉ ጊዜ ፀሀፊ በመሆን ስራዎቼን እየሰራሁ እገኛለሁ፡፡ • ከ500 በላይ የግጥም መድረኮች ላይ ስራዎችን አቅርቢያለሁ፡፡ • ከአለም ከተውጣጡ ገጣሚያን ጋር በጋራ የግጥም ስራዎቹን ሀገሩን ወክሎ አቅችቢያለሁ፡፡ • በኢቢኤስ ሀበሻ ዊክሊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቻለሁ፡፡ • ግሎባል ሳውንድ የራዲዮ ፕሮግራም ተባባሪ አዘጋጅቻሀለሁ፡፡ • አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል የስነ-ፅሁፍ ክፍል ኃላፊ ሆኜ ሰርቻለሁ፡፡

Books by ሰለሞን:

ያማል!

ያማል!

Poetry, Literature

የልብ ማሕተም

የልብ ማሕተም

Fiction, Poetry, Literature