ያ‘ፍቃሪ ሰው ትንፋሽ

ያ‘ፍቃሪ ሰው ትንፋሽ

Author/s: ሰለሞን ሳህለ

Subjects

Literature, Poetry

Published Year

መጋቢት 2013 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ፍቅር እያለን የሌለን ያህል ሆኖብናል፡፡ እየፈለግነው ርቀነዋል፡፡ በግርግሩ መሃል በናረ ጩኸት ሰክረን እንዳልጠና ግልገል ርምጃችን ሁሉ መውደቅና መውተርተር ሆኗል፡፡ ናላችንን ያዞረው የግርግሩ የዞረ ድምር ዐይናችንን አጨናብሶት እርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ራሳችንንም እንዳናይ ጋርዶናል፡፡ አለመተያየታችን አላደማመጠንም አለመደማመጣችን አላግባባንም አለመግባባታችን ፍቅራችንን አርቆብናል፡፡ ኑ እና በሕብረት ፍቅርን እንፈልገው. . . መፈለጉን ከራሳችን እንጀምረው. . .ስናገኘው እንተንፍሰው ስናገኘው እንኑረው. . . ለሌሎችም እናሳየው. . . ያኔ በግርግሩ ጉልበት የተገነባውን በናረ ጩኸት የተለሰነውን. . .ያለመደማመጥ ግንብ እንንደዋለን፡፡“ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ” የግጥም መድብልም የዚህ ፍለጋ አንድ አካል ነው፡፡ እያንዳንዷን የፍቅር ትንፋሽ እያሰቀጠሉ መኖር፡፡ . . . ጥፋታችንን በፍቅር እናርመዋለን ሕመማችንን በፍቅር እናክመዋለን፡፡ የሕይወትን ውስብስብ ቋጠሮ በፍቅር ብልሃት መፍታት እንችላለን፡፡ ከተሰጡን ትልቅ መሰጠቶች ሁሉ ኃያሉ ፍቅር ነው፡፡ በእርሱም ሁሉን መከወን እንችላለን፡፡ “ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ” ይህን መንገድ ጠቋሚ ቀስት ነው እያንዳንዱ ፍላፃ የፍቅር ትንፋሽ ነው. . . ሕይወት እንድትረዝም እስትንፋሱ መቀጠል አለበት፡፡ ደግሞ ደጋግሞ ፍቅርን መኖር አሁንም አሁንም ሳያቋርጡ ፍቅርን መተንፈስ፡፡ ይሄ ነው “ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ” በሙሉ ልቤ እየተነፈስኩት ነው. . . ከፍቅር በላይ አንዳች የለምና ኑ እና አብረን ፍቅርን እንኑረው ኑ እና እንዋደድ እየተዋደድን አብረን ፍቅርን እንተንፍሰው. . .

0.0 (0 reviews)