ዶ/ር ታደሰ ብሩ ኬርስሞ

ዶ/ር ታደሰ

ታደሰ ብሩ ኬርስሞ በኢትዮጵያ በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ በሙሉ ጊዜ፤ በትርፍ ጊዜው ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ድህረ ምረቃ በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን አስተምሯል። በእንግሊዝ አገር ግሪንዊች ዩኒቨርስቲና ካፕላን ኢንተርናሽናል ኮሌጅን ጨምሮ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቢዝነስ እና የማኔጅመንት ኮርሶችን አስተምሯል። ኢትዮጵያ ውስጥ አጫጭር ሥልጠናዎችን በመስጠት ይታወቃል። በኢሳት ቴሌቪዥን ይተላለፍ የነበረው "የትምህርት ብልጭታ" የተሰኘው ትምህርታዊ ፕሮግራሙ ከሕዝብ ጋር ይበልጥ ያስተዋወቀው ነው። ታደሰ ብሩ ኬርስሞ በኢኮኖሚስክ በከፍተኛ ማዕረግ የማስትሪት ዲግሪ ያለው ሲሆን በማኅበራዊ ሳይንሶች የዶክሬት ዲግሪ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት አጠናቋል። ከዚህም በተጨማሪ በሰላም፣ ቅራኔዎችና ዲፕሎማሲ በከፍተኛ ማዕረግ የማስትሬት ዲግሪ አለው፣ በዚሁ መስክ ለተጨማሪ የዶክሬት ዲግሪ እየሠራ ይገኛል።በእንግሊዝ አገር በዲሞክራሲ፣ የህግ የበላይነት እና ሲኩሪቲ ፊሎውሺፕ ተከታትሏል። በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ በወጣቶችና ማኅበራዊ ዕድገት ላይ ለሚሠራ አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በኤክስፐርትነት ያገለግላል።ደራሲውን በዚህ አድራሻ ማግኘት ይቻላል tkersmo@yahoo.com.

Books by ዶ/ር ታደሰ:

የሥራ አመራር ጥበብና ተያያዥ ጉዳዮች

የሥራ አመራር ጥበብና ተያያዥ ጉዳዮች

Management, Communication, Leadership, Non Fiction

ተከታይነት

ተከታይነት

Management, Communication, Leadership, Non Fiction