የሥራ አመራር ጥበብና ተያያዥ ጉዳዮች

የሥራ አመራር ጥበብና ተያያዥ ጉዳዮች

Author/s: ዶ/ር ታደሰ ብሩ ኬርስሞ

Subjects

Management, Communication, Leadership, Non Fiction

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ዶ/ር ታደሰ ብሩን ካወቅኩት ወደ አራት ዓመታት ያህል ሆነኝ:: በእነዚህ አራት ዓመታት ውስጥ የሱን የማኔጅመንት ሣይንስንና የሌሎችን የሙያ ዕውቀቶችን አቀላቅለን ለብዙ ችግሮች መፍትሄ የሰጠንባቸው ፕሮጀክቶች አብረን ሠርተናል። በእነዚህ የሥራ ወቅቶች ስለዶ/ር ታደሰ ከሁሉም በላይ የተገነዘብኩት ምንያህል "ተፈጥሯዊ" መምህር እንደሆነ ነው:: "ተፈጥሯዊ" የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት የዶ/ር ታደሰን በታላቅ ትዕግሥት የማዳመጥ፣የመመራመርና ከሁሉም በላይ ደግሞ ሃሳቦችን በቀላሉ የማቅረብና የማስረዳት ችሎታን ለመግለጽ ነው። በጣም የሚገርመኝ ደግሞ ይህንን የሚያደርገው ሃሳቡን የሚያቀርብባቸው የዕውቀት ዘርፎች ብዙም የመማሪያም ሆነ የምርምር ውጤቶች ባልተፃፈበት በአማርኛ ቋንቋ መሆኑ ነው። ይህ "ተፈጥሯዊ" መምህር ያልኩት ሰው በዚህ የሥራ አመራር ጥበብ እና ተያያዥ ጉዳዮች ብሎ በሰየማት መጽሃፉ ውስጥ ስለውጤታማ ግለሰብ፣ ድርጅትና አመራር ዘመኑ የደረሰበትን ዕውቀት፣ ምርምርና ልምዶች በአንድ ቦታ ሰብስቦና ለኢትዮጵያውያን በሚያመች መልኩ በአማርኛ ቋንቋ አቅርቧል። የዚህ መጽሀፍ ይዘት የዓለማችን ታላላቅ ኮርፖሬሽኖችን፣ የሚሊታሪ ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም በግል ሥራ የተሰማሩ ሰዎች አሠራራቸውን ፍሬያማ ለማድረግ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መድበው ሠራተኞቻቸውን የሚያሰለጠኑበት ትምህርት ነው። ስለዚህ ይህች መጽሀፍ ለሚያነባት ሁሉ በየተሰማሩባት ሙያና ሥራ ከድካማቸው አመርቂ መልስ ለማግኘት በግለሰብ ጥንካሬ፣ በቡድን ግንባታ፣ በአመራርና በውሳኔ አሰጣጥ ዙሪያ ያሉትን ስትራቴጂያዊና ዘመናዊ ዕውቀቶችን ለመተዋወቅ በርከፋች ነች። መጽሀፏን ማንበብብቻ ግን በቂ አይደለም። ማጥናትና ከሁሉም በላይ ደግሞሥራ ላይ ለማዋል አዘውትሮ መሞከርንም ይጠይቃል። አዚዝ መሀመድ (ዶ/ር) ሲንየር ቴሌኮም ሪሰርች ሳይንቲስት አልካቴል - ሉሰንት ይህ "የሥራ አመራር ጥበብ እና ተያያዥ ጉዳዮች"የተሰኘው፣ አራት ክፍሎችና አስራ ዘጠኝ ምዕራፎች ያለው የዶ/ር ታደሰ ብሩ መጽሐፍ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ ያሉ መሪዎችን የሚያጎለብቱ ጠቃሚ ትምህርቶችን ይዟል። እነዚህ ትምህርቶች በራስ መተማመንን ለማጎልበት፤ ድርጅታዊ ብቃትን ለማጎልበት እና ውጤታማ መሪ ለመሆን የሚረዱ ናቸው። መጽሐፉ በአማርኛ ቋንቋ መፃፉ ደግሞ የአገራችን የቢዝነስ ሰዎችን፤ የማኅበረሰብና የድርጅት መሪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መጥቀም የሚችል እንዲሆን አድርጎታል። ዶ/ር ታደሰ ውስብስብ ጽንሰ-ሀሳቦችን በቀላል አቀራረብ መግለጽ የሚችል ባለሙያ መምህር ነው። የብዙ ዓመታት የመምህርነትና የአሰልጣኝነት ልምዱ በዚህ መጽሐፍም ውስጥ በጉልህ ይታያል። በግል ሕይወታቸው፣ በድርጅቶቻቸውና በማኅበረሰባቸው ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚፈልጉ ሁሉ ይህንን መጽሕፍ እንዲያነቡ እመክራለሁ። ዶ/ር አሰግድ ሀብተወልድ አሰልጣኝ እና አማካሪ Success Pathways, LLC ዩ. ኤስ. አሜሪካ ዘመኑ በሚጠይቀው ንድፈ-ሀሳቦችና የአፈጻጸም ስልቶች ያልታነጹ መሪዎችና ድርጅቶች ውጤታማ መሆን ያዳግታቸዋል። በዘመናዊ የሥራ አመራር ንድፈ ሀሳቦች ፤ መርሆዎችና፣ አፈጻጸም ስልቶች የሚመሩ ውጤታማና ስኬታማ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለማንኛውም ኅብረተሰብ ቀጣይ እድገት ወሳኝ ናቸው። የፓለቲካ፣ የሲቪክ፣ የንግድ ድርጅቶች፣ ለማደግ፤ ለማበብ ብሎም ለሚገኙበት ኅብረተሰብ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ከዘመናዊ የሥራ አመራር ንድፍ ሀሳቦች ፣ መርሆችና በተግባር የተፈተኑ አፈጻጸሞች ትምህርት መቅሰም አለባቸው። አመራር፣የለውጥ ማኔጅመንት፣ የሚማር ድርጅት፣ አፈጻጸም፣ ማኅበራዊ ካፒታልና ወዘተ... በመጽሃፉ የተካታቱ ርእሰ ጉዳዮች በዘመናዊ የሥራ አመራር ሣይንስና ተዛማጅ ዲስፕሊኖች በኅብረተሰቦች ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ድርጅቶችን አስተሳስብና አፈጻጸም የለወጡ ግዙፍ የምርምር ስራዎች የተጻፉባቸው ርዕሶች ናቸው። ዶ/ር ታደሰ በቀላል አቀራረብና በአማርኛ ቋንቋ እነዚህን ሁሉ ውስብስብና ስፋፊ ንድፈ ሀሳቦችና መርሆዎች አቅርቦልናል። የነግላድዎልን፣ ጆን ኮልንስ፣ ዲስቶ፣ ሲንግና የሌሎችም የእውቀት ወጎች(ዲስፕሊኖች) ግዙፉን የእውቀት ምርቶች ጭማቂ በአማርኛ ቋንቋ ተፍታተው ማንበብ የእነዚህን ምሁራንና ተመራማሪዎች ጽንሰ ሃሳቦችና አስተምሮቶች ላነበበ ሰው እንኳን በራስ ቋንቋ ደግሞ ማንበብ የአስተሳሰብ ጥራትና መስላት የሚያዳብር ነው። በሁሉም ዓይነት ድርጅቶች ውስጥ በኃላፊነትም ሆነ ከኃላፊነት ውጭ ለሚገኙ ዜጎች "የሥራ አመራር ጥበብ እናተያያዥ ጉዳዮች" በማንበብ፡ በቋንቋ አቀራረቡ እንደሚረኩ፤ በትምህርቱም እንደሚጠቀሙ ተስፋ አደርጋለሁ። ነአምን ዘለቀ የኢሳት ማኔጂንግ ዳይሬክተር

0.0 (0 reviews)