ተከታይነት
Summary
ቆም ብሎ ለማሰብ ዕድል በማይሰጥ ውክቢያ ውስጥ በተለመደው ክብ ውስጥ እየተሸከረከርን ከምናልፋቸው ጉዳዮች አንዱ ሳይሆን አይቀርም ተከታይነት! ኃላፊነትን በልህቀት ለመከወን የአንድን ጉዳይ መነሻሃ ሀሳብና ምንነት በቅጡ መረዳት አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ በዚህ መፅሀፍ ውስጥ ያየሁትም እየሄድን ስለምናስብ ልብ ከማንላቸው ጉዳዮች አንዱ የሆነውን የተከታይነት ሃሳብ ነው፡፡ መሪው ዓላማው ላይ ሳያተኩር ተከታይም መሪውን ሳይከተል መሪውም ዓላማውን ተከታዩም መሪነትን አያሳካም ብዬ እንዳስብ አድርጎኛል፤ደግሞም ዝም ብሎ መከተል ሳይሆን የተከታይነትን ዋጋና ልክ በቅጡ ተረድቶ መሆን እንዳለበት እንድናይ የሚያደርግ ፅሁፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ድል፣ስኬት፣ካሰቡት መድረሰ እና ውጤታማነት ለመሪው ብቻ የሚተው አክሊል ሳይሆን ተከታይና መሪው የሚጋሩት የጋራ ክብር መሆኑን ከቀልባችን ሆነን እንድናስብ በርከፋች የሆነ ስራ ነው እናም ሰለተከታይነት ብዙ ያሳስባል ብዙ ያስብላል። ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኝወርቅ