ዮናስ አለማየሁ

ዮናስ

ዮናስ አለማየሁ እባላለሁ፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በ19 98 ዓ.ም. በ MIS (Management Information System) የትምህርት ዘርፍ ወስጃለሁ፡፡ በ2002 ዓ.ም. ወይም 2010 (እ.አ.አ.) ደግሞ Victory Bible College በ "Practical Theology" ዲፕሎማ አግኝቻለሁ፡፡ ከልጅነቴ አንስቶ መጽሐፍ ማንበብ እወድ ነበረ፡፡ በቻልኩት መጠን ሳነብ ነው ያደግሁት፡፡ ታላቅ ወንድሜ ዶክተር ዘውዴ አለማየሁ መጽሐፍት እና ማንበብ ላይ እንዳተኩር መልካም ተጽእኖን በላዬ ላይ አኑሮብኝ ኖሯል ብዬ እላለሁ፡፡ እናም ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ብዬ አምናለሁ፡፡ ነጮቹ "readers are like a tonic" ብለው እንደሚሉት ማለት ነው፡፡ የተለያዩ መንፈሳዊና ዓለማዊ መጽሐፍትን በመተርጎም ዳጎስ ያለ ልምድን አካብቻለሁ፡፡ ከእነዚህም መካከል በጥቂቱ፡- - በመንፈሳዊነት ማደግ (Kenneth E. Hagin) - የአማኙ ሥልጣን (Rev. Kenneth E. Hagin) - በእግዚአብሔር መንፈስ እንዴት መመራት ትችላላችሁ ? (Rev. Kenneth E. Hagin) - መፈወስ ትችላላችሁ (Pr. Billy Joe Dougherty) - የእምነት ኃይል (Pr. Billy Joe Dougherty) - የጸሎት መርሆዎች (Pr. Billy Joe Dougherty - ሁለት ዓይነት ጽድቅ( Essec William kenyon) - ከመስቀሉ እስከ ዙፋኑ( Essec William kenyon) - አንድነታችን (Essec William kenyon) - ሕይወት ምርጫ ነው (Dr. Robert Anthony) - ምትሃተኛው የዛፍ ላይ ቤት (children’s books) by Mary Pope Osborn ጌታ ቢፈቅድና ብኖር በቀጣይም ሌሎች በርከት ያሉ የትርጉም እንዲሁም የራሴን ወጥ ሥራዎች ለተደራሲያኑ እንደማበረክት ለራሴ ቃል እገባለሁ፡፡ ዮናስ አለማሁ

Books by ዮናስ:

ሕይወት ምርጫ ነው

ሕይወት ምርጫ ነው

Non Fiction, Self development