አንዷለም አራጌ

አንዷለም

ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ጥቅም 25 1965 ዓ.ም ደብረ ታቦር ወጣ ብላ በምትገኘው ክምር ድንጋይ ተወለደ። የመጀመሪያ ዲግሪውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት ክፍል አግኝቷል። በአሁኑ ስዓትም በፖለቲካል ሳይንስ ኮምፓራቲቭ ፖለቲክስ የትምህርት መስክ ሁለተኛ ዲግሪውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተከታተለ ይገኛል። አንዷለም አራጌ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዋጋ ከከፈሉ እና ስማቸው ከሚጠቀሱት ሰዎች ግንባር ቀደሙ ነው። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ፓርቲ(ኢዴፓ) ውስጥ ከፈተኛ አመራር በመሆን አገልግሏል። በኋላም የ1997 ምርጫን ተከትሎ ከመጣው የቅንጅት አመራር ውሥጥ አንዱ ነበር። በወቅቱም በፖለቲካ እስር የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ነበር። በኢትዮጵያ የተመሰረተው የአንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትሕ ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ በመሆን ሰርቷል። አንዷለም ከታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ከተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እና ጋዜጠኞች ጋር መስከረም 4 ቀን 2004 ከታሰረ በኋላ በሽብርተኝነት ተከሶ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ነበር። በወቅቱ የእሱ መታሰር በሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተቃዋሚዎችን ለመጨፍለቀ የተደረገ ሲሉም ድርጊቱን ኮንነውት ነበር። ከ3 ዓመታት በፊት 7 ፓርቲዎች ተዋህደው በፈጠሩት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ ምክትል መሪ በመሆን አገልግሏል። ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ በእስር ቤት ቆይታው በነበረበት ወቅትም 4 መፅሐፎችን በመፅሐፍ ለንባብ አብቅቷል። "ያልተነበበው አንባቢ" የተሰኘው ስራው 5ኛ መፅሐፉ ነው።

Books by አንዷለም:

ያልተነበበው አንባቢ

ያልተነበበው አንባቢ

Biography, Self Development, Non Ficition