ያልተነበበው አንባቢ

ያልተነበበው አንባቢ

Author/s: አንዷለም አራጌ

Subjects

Biography, Self Development, Non Ficition

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

አሁን ግን ገና ባልጠና ዕድሜው ሌላ ያልተዘጋጀበት እሳት ወረደበት። የአቶ ባልቻ ቤተሰብ ገጠር በደረሰ በሦስተኛው ዓመት ሌላ የከፋ ዱብ እዳ ገጠመው። ወ/ሮ እታቱ ልጆቿን ለመጠየቅ ወደአዲስ አበባ አበባ ተመልሰው ነበር። ታዳጊው ነጋሽ ከአባቱ ጉያ ሳይርቅ አባቱ ነጠና ታመሙበት። በጭንቀት ተሰቅዞ ተያዘ። እርሱ መፍትሔ መስጠት ቢያቅተው መፍትሔ አያጡም ያላቸውን ዘመዶቻቸውን በር አንኳኳ። ዘመድም ከእያቅጣጫው ተጠራርቶ ተሰባሰበ። የቤቱ ምሰሶ አታቱ የወላድ አንጀት አልችል ብሏቸው ወደ አዲስ አበባ ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ሲሄዱ የሕይወት ሌላው ድንገተኛ መከራ ወረደባቸው። የሕይወት ዘመን ውሃ-አጣጫቸውን ስምንት ልጆቻቸውን የነጠቃቸው መላከ-ሞት የልጆቻቸውን አባትም ለመንጠቅ ሌላ ፍልሚያ ከፈተባቸው። የአቶ ባልቻ ዘመዶች ወንድማቸው እንደማይተርፉ ሳይገምቱ አልቀሩም። በጠዋት በማታ ተራ ገብተው ታስታምሟቸው ጀመር። የህክምና አለመኖር ካልሆነ በስተቀር ህመማቸው ብዙም ከባድ የሚባል አይመስልም ነበር። ሆኖም አቶ ባልቻን በዘመድ አዝማድ ርብርብ ብቻ ማትረፍ አልተቻለም። ታዳጊው ነጋሽ ገና በለጋ ዕድሜው ከልብ የሚወዳቸውንና የሚመካባቸውን አባቱን በሞት ተነጠቀ። እንደ አዋቂዎች አልቅሶ አይወጣለትም: ስብራቱን ግራ መጋባቱ ደግሞ ከፍ ያለ ነው። ሰማይ የተደፈሰበት ታዳጊ ሆነ። የተደፋበትን ሰማይ ከላዩ ያነሱለት ዘንድ የእናቱ የወ/ሮ እታቱን ከአዲስ አበባ መመለስ በሃዘን ተቆራምዶ መጠበቅ ግዴታው ሆነ። *** አንዳች ሳያንገራግሩ ታሪኩንም ልየው ሳይሉ ቀረፃውን እንድናካሂድ ፈቀዱልን። እንዲሁ በእምነት ተባበሩን ቢሮቸውን ሙሉ በሙሉ ነው የለቀቁልን። በወቅቱ ደግሞ በጣም ስራ የሚበዛባቸው ወቅት ነበር። እንዲህ እንዳሁኑ እረፍት ላይ የነበሩበት ወቅት አልነበረም። እና የእርሳቸውን ቢሮ ተጠቅመን ስንቀርፅ፣ እሳቸው ኮሊደር ላይ ቁጭ ብለው ሲፅፉ አስታውሳለሁ። እና ሁኔታቸው በጣም ያስጨንቀን ነበር።በተለይ አበበ ባልቻ "እኒያ ሰውዬ እዚያ ቁጭ ብለው እኔ አረዚህ አረንዴት ነው የምሰራው? እኔ በጣም እየከበደኝ ነው" እያለ በጣም ይጨንቀው ነበር። ከዚያ ከእርሳቸው ጋር ወዳጅ ሆኑ። እንዲያውም አንድ ቀን የማስታውሰው ተንደርድሮ ሂዶ ጉንጫቸውን ነው የሳማቸው። በቃ እንደዚህ አይነት ኢትዮጵያዊ: እንዲህ አይነት ሰው ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ እንዲህ አይነት ልብ ያለው ሰው መገኘቱ ብሎ በአድናቆት ጉንጫቸውን ሳማቸው። እርሳቸውም በሁኔታው ስቀው" አሁን እኔን እዚህ ጉንጨን ትስማለህ: ማታ ደግሞ ሰው ስታሰቃይ ታድራለህ ብለው መለሱለት። *** ሞት በአካል መነጠል ነው። ሞት ከአጭር የህላዌ ውጣ ውረድ ህልቆ መሳፍርት ወደሌላቸው የዘላለም ዓመታት መንጠቅ ነው። ሞት ከሚያውቁት ወደማያውቁት ዓለም መቅዘፍ ነው። ሞት በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ደጋግሞ ቢሸነፍም። የመጨረሻውን የድል ፅዋ የሚያነሳው ግን ሞት መሆኑን እርሱም ያውቃል። እኛም እናውቃለን። ሞት ነጋሽ ባልቻን በተለያየ መንገድ ተፋልሞታል። ሲያሻው በካንሰር፣ ሲያሻው ረጅም ሰዓታት በሚፈጅ ቀዶ ጥገና አልሆን ሲለው ደግሞ በኮቪድ -19 በመጠቀም ነፍሱን ለመንጠቅ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ አድርጓል። ነጋሽ ሁሉንም በድል አድራጊነት ተወጥቷል። ነጋሽ ከፍ ያለውን የስነ -ልቦና አይበገሬነት በመጠቀም ሞትን ደጋግሞ ወደመጣበት መልሶታል። ነገር ግን ሞትን ደጋግመን ድል መንሳታችን ሞትን ጨርሶ የሚያበቃ ኃይል አያጎናፅፈንም። ሞትን በረታንበት ቅፅበት እንኳ አንድ ቀን የሞት ሰለባዎች እንደምንሆን እናውቃለን። የሞት ሰለባ ከምንሆንበት ቀን ጋር መቼ እንደምንገናኝ አለማወቃችን ግን ሞትን የማይቀምሱ መላዕክትን ያህል ዘና ብለን እንድንኖር ያደርገናል።

0.0 (0 reviews)