ሲራክ ወንድሙ

ደራሲና ገጣሚ ሲራክ ወንድሙ ታህሳስ 8/ 1993 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚዛን ተፈሪ ተወለደ። አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚዛን አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታሏል። በአሁኑ ሰዓትም በወራቤ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን እየተከታተለ ሲሆን በሳምንታዊው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የተለያዩ መጣጥፎቹን እያስነበበ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር ወርሃዊ የ digital platform ባላቸው መፅሄቶች ላይ በመሳተፍ ይታወቃል። የስነ ፅሁፍ ዝንባሌው ጋር ከልጅነቱ ጋር የተዋወቀው ወጣቱ በርካታ ያልታተሙ መፅሀፍት ባለቤት ሲሆን አዘቦት የሚል ርዕስ በ postcard story ዘውግ መፅሀፉን ሲያሳትም የመጀመሪያው ነው።