አዘቦት

አዘቦት

Author/s: ሲራክ ወንድሙ

Subjects

Fiction, Postcard History

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1869 ዓ.ም በሀገረ ኦስትሪያ እንደተጀመረ የሚነገርለት የፖስት ካርድ ታሪክ ፅሁፍ አውሮፓን ለማጥለቅለቅ ብዙም ጉልበት ፈላጊ አልነበረም። ብዙ የሚባሉ ግዛቶች ላይ እንደክረምት ጎርፍ እየተገማሸረ የስነ ፅሁፍ አንድ ወገን ሆኖ እንዲወለድ ውለታ ዋለ። ይህ ማለት እንግዲህ ዘመኑን በእኛ ሀገር ስንመነዝረው ከአድዋ ድል በፊት ከአፄ ቴዎድሮስ ሞት ወዲህ ማለት ነው። እንደአለመታደል ሆኖ ግን ይህ ቅርፅ እንደአንድ የስነ ፅሁፍ አካል ሆኖ ለመገኘት በሀገራችን አሳር የሚበዛበት ይመስለኛል። መፅሀፍት የግድ እንደነፍቅር እስከ መቃብርና ወንጀለኛው ዳኛ ደጎስ ካላለ ለሚሉ ወገኖች የሁለት መስመር ድርሰት ስራ መፍታት ነው። ኢትዮጵያ እና የፖስትካርድ ታሪክ ጅማሮው ይህ ነው ብሎ ለመዘርዘር ራሱን የቻለ ትልቅ ጥናት ቢጠይቅም በተለይ የማህበራዊ ሚድያው በዚህ ልክ ለቀቅ ማለትና በስነፅሁፈኛ ወጣቶች መተኮር በአሁኑ ሰዓት የመነቃቃት ስሜቱ በጥሩ አነሳስ ላይ እንዳለ እታዘባለሁ። ሆኖም ግን ጅማሮውን እንደጅማሮ መቀበል ካልሆነልን በቀር የዚህን ያህል ዘውጉ በብዙ ዳብሯል ለማለት አያስደፍርም። አሁን ላይ ያለው ወጣቱም ዘመን በሰጠው የቴክኖሎጂ በረከት እየታገዘ ቢያሶሞሱም በጅማሮው ላይ ላለው ዘውግ ብርታት ይሆናል ብዬም በፅኑ አምናለሁ። አዘቦት በሚል ርዕስ ለንባብ የቀረበው የገጣሚና ደራሲ ሲራክ ወንድሙ መፅሀፍ ይህንኑ በጅምር ላይ ያለውን የስነ ፅሁፍ ዘውግ ወደፊት ለማስቀጠል አንድ ምዕራፍ ነው። አዘቦት የአጭር አጭር ( postcard history ) ዘውግ ያላት መጠነኛ መፅሀፍ ስትሆን የተለያዩ ዘመን የወለዳቸውን የስሜት ፣ የልብና የነፍስ ጩኸት ጥንቅሮችን ሰንዳ ቀርባለች። በቀጣይም ከአዘቦት በተሻለ የሚመጡ እኔን መሰል ወጣቶች ይህን ቅርፅና መንገድ ቢያዳብሩት ብዬ አስባለሁ። ሰው ዘመኑን ፣ ትንፋሹን ፣ ባህልና ውዳሴውን ሲመስል እንዲህ ይቃኛል። አዘቦትም በውስጧ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ግላዊ ተብሰልስሎት ያረፈባቸው ቀለሞችን በውስጧ ሰንዳለች። በዚህ መፅሀፍ ውስጥ የተቀመጡ እያንዳንዳቸው ፅሁፎች የሰርክ የሰርክ የኑረታችን እህታዎች ሳይሆን ተለምዷዊ አዘቦታዊ ደብዛዛ ቀለም ያጠላባቸው ንግግሮሽ በጊዜ ምጣድ ላይ ተጥዶ የሚበስሉበት ነው።

5.0 (1 reviews)