ይኸነው ጌታቸው

ይኸነው

ይኸነው ጌታቸው በቀድሞ መጠሪያው ጋሞ ጎፋ ዞን በመባል በሚጠራው አካባቢ ውስጥ በምትገኘው ሳውላ ከተማ በመስከረም 1976 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን እድገቱም በአሁንዋ የጋሞ ዞን መናገሻ በሆነችው አርባ ምንጭ ከተማ ነው፡፡ የአንደኛ እና መለስተኛ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ ኩልፎ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም በአርባ ምንጭ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ለመከታተል በቅዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪውን በታሪክ ትምህርት ከጂማ ዩኒቨርሲቲ መከታተል ችልዋል፡፡ በተለያዩ የግል ት/ቤቶች በታሪክ መምህርነት ከ14 ዓመት በላይ ለማገልገል ከመቻሉም በተጓዳኝ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እገዛ የምያደርጉ አጋዥ መጽሀፍትን በማዘጋጀት ተደራሽ ለማድረግ በቅቷል፡፡ ጎን ለጎንም በድህረ-ገጽ አምካኝነት የመሰናዶ ተማሪዎችን ለዩኒቨርሲቲ ፈተና ብቁ ለማድረግ በማለም ብርቱ ተግባር በመከወን ላይ ከሚገኘው ኢድሁብ ተቋም ጋር በመስራት የራሱን ሚና ለመጫወት ችልዋል፡፡ ከሙያ አጋሮቹ ገር በመተባበር ስኩል ኦፍ ኢትዮጵያ የተባለ ትምህርት ቤት በመመስረት ለበርካታ ዜጎች ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን የራሱን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ ስለ ሰብ በሚል ርዕስ በዚሁ ድህረ-ገጽ ለተደራሲያን የቀረበው ይህ መጽሀፍ በስነ-ህዝብ ጉዳይ ላይ የምዕራባዊያን ሀገራት የሚከተሉትን በሴራ የተሞላ ፖሊሲ ከተሟላ መረጃ ጋር በማስደገፍ ትንተና ይሰጣል፡፡

Books by ይኸነው:

ስለ ሰብ

ስለ ሰብ

Politics, Non Fiction