ስለ ሰብ

ስለ ሰብ

Author/s: ይኸነው ጌታቸው

Subjects

Politics, Non Fiction

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ሀያላኑ ሀገራት እንዴት ባለ መንገድ ጦርነትን የስነ ህዝብ ፖሊሲያቸዉ ማስፈጸምያ በማድረግ እንደሚጠቀሙበት በዝርዝር የሚፈትሽ መጽኃፍ ነዉ፡፡ በመጽሃፉ ዉስጥ ጦርነትን የሀያላን ፤የሀያላንና ደካማ ሀገራት ፤የደካማ ሀገራት ፤የእርስ በርስ ጦርነት እና ጅምላ ፍጅት ወይም የዘር ማጽዳት በማለት በመከፋፈል በእያንዳንዱ ክፍል ዉስጥም ምሳሌዎችን በመስጠት ዘርዘር ያሉ ጉዳዮችን ይዳስሳል፡፡ በአለም ላይ በተለያየ መልክ የሚከሰቱት ግጭቶች በሽታዎች በመንግስትም ይሁን በሌሎች ጣልቃ ገብነት የሚተገበሩ (በተለይም በማደግ ላይ ባሉ ሶስተኛዉ የአለም ሀገራት )የስነ ህዝብ ፖሊሲዎች ምግብ እና ምግብ ነክ በሆኑ ተዋጽኦዎች የሚከሰቱ የጎንዮሽ ጉዳቶች ወዘተ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሃያላኑ ሀገራት በሚቀረጹ የስነ ህዝብ ፖሊሲዎች ዳብረዉ የሚዘመሩ ስለመሆናቸዉ ከበቂ ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማብራርያ የሚሰጡ ነጥቦች ከተለያዩ ክፍለ አለማት ምሳሌዎችን በማንሳት በመጽሃፉ ዉስጥ ለማስቀመጥ ሙከራ የተደረገ ሲሆን የተነሱት ሀሳቦች ግልጽ እና ሳቢ ናቸዉ ለማለት በሚያስደፍር መጠን ለማብራራት የተሞከረ ሲሆን ለተነሱት ነጥቦችም ስለ ተኣማኒነታቸዉ ዘርፈ ብዙ ከሆኑ ታማኝ የመረጃ ምንጮች መፈተሽ እና ማመሳከር ተደርጎባቸዋል ፡፡ የምንኖርባት መሬት በተፈጥሮ የተቸረች ሀብት በዉስን መጠን መገኘቱ በፍጥነት እያሻቀበ መሄድ ላይ በሚገኘዉ የህዝብ ቁጥር ላይ ማስተካከያ ማድረግ አስገዳጅ እንዲሆን አደረገ፡፡(እዚህ ላይ የህዝብ ላይ የህዝብ ቁጥር ጭማሪ ለሁሉም ሀገራት በእኩል ደረጃ ራስ ምታት እናዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ፡፡)ተግዳሮቱ ካላቸዉ ዉሱን የተፈጥሮ ሀብት በተጨማሪነት የኢኮኖሚ አቅማቸዉ ደካማ በመሆኑ መነሻነት 3ኛዉ የአለም ሀገራት በመባል በሚታወቁት በማደግ ላይ ባሉት ሀገራት ጫናዉ ጉልህ እንዲሆን አድርጓል፡፡በኢኮኖሚ የበለጸጉ ሀገራት በአለም ላይ በሚከተሉት ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖሊሲ መነሻነት ጥቅማቸዉን በቀጣይነት ለማስጠበቅ ደካማ በሆኑት ሀገራት ጭምር ረጅም እጃቸዉን በማስገባት የስነ ህዝብ ፖሊሲያቸዉ ከሀገሪቱ ዓላማ በተጨማሪ የኃያላኑን ፍላጎት ባማከለ መንገድ ሳይወዱ በግዳጅ እንዲተገብሩ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

5.0 (1 reviews)