ኢሳያስ ባንጫ

ኢሳያስ

ኢሳያስ ባንጫ በ ኢ.አ 1991 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ የተወለደ ሲሆን የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም በወላይታ ሶዶ አይነስውራን ት/ቤትና ሶዶ ቀለምና መሰናዶ ተከታትሏል። የከፍተኛ ትምህርቱንም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማረ ሲሆን በቋንቋና ስነጽሁፍ በድግሪም ከዩኒቨርሲቲው ተመርቋል። የሁለተኛ ድግሪውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና በተመሳሳይ ደግሞ በዲፕሎማሲና አለምአቀፍ ግኑኝነት በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የሚገኝ; በእኚህም እጩ ተመራቂም የሆነ፤ የሃያ አምስት አመት ወጣት ነው። ስሜትና ስሌት፣ ምናብና ምንባብ፣ ሃቅና ሳቅ እንዲሁም ንቅሳትና ትኩሳት የተሰኙ ሁለት የግጥምና ሁለት የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ የሆኑ አራት መጽሃፍትን ለአንባቢያን አድርሷል። የመጽሃፎቹ ጥቅል ይዘት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ፍልስፍናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ድርሰቶቹን ግን ልዩ የሚያደርጋቸው በኢትዮጲያ የስነጽሁፍ እና ኪነጥበብ እንቅስቃሴ ውስጥ ብዙም ቦታ ያልተሰጠውን የአይነስውራንን የፍቅርና ተያያዥ የህይወት መልኮች ብሎም ከሌሎች ማህበረሰቦችጋር ያላቸውን ግኑኝነት ለዛ ባለው ትረካና የአጻጻፍ ስልት ሳቢነትን አላብሶ ማቅረቡ ነው።

Books by ኢሳያስ: