ምናብ እና ምንባብ
Summary
የንባብ ብቻ ሳይደል ከራስጋም መታረቂያ ከሆነው፤ ስድስት ኪሎ ከየካቲት አስራሁለት ሆስፒታል ጀርባ፤ ዝቅ ብሎ ከሚገኘው፤ ዞን ላይብሬሪ እያነበብኩ እንደቆየሁ እወጣለሁ። የሀሩሩ መፋጀት ምድርን ምጣድ እኛን ቆሎ አድርጎ ሊቆላን የቆረጠ ይመስላል። ድንገት እያዘገምኩ ቆም ብዬ ስልኬን ከኪሴ አወጣሁት። ሰአቱን ለማወቅ ነበር። ስምንት ሰአት ተኩል ይላል። በጊዜው የሚያጣድፈኝም ነገር ኖረ የሚጠብቀኝ ሰው ስለሌለ አከባቢውም ነጻ ስለነበር ኬኔን አጥፌ ጀነን እያልኩ መራመድ ጀመርኩ።