ድራጎን በኢትዮጵያ ሰማይ
Summary
ድራጎን በኢትዮጵያ ሰማይ በሌሊት ሰዓት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ስለሚያንዣብቡ የዓለም የደህንነት ሳታላይቶች፤በኢትዮጵያ ምድር ላይ የተሰማሩ የጥናት ባለሙያዎች፤ከሳታላይቶች ጋር ያላቸውን ጥብቅ ግንኙነት፤የድራጎን (ዘንዶው) አሰራሮች በሀገራችን ላይ እንዴት እየረቀቁ እንደሆነና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሕጻናት ሳይንቲስቶችን እንዴት እንደሚፈለጉና ዕውቀታቸውን እንዴት ለዓለሙ ሁሉ እንደሚያስፈልግ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘንዶውን ሀሳቦች መቀበል እንደማትችልና ሁሉጊዜም ጠላቶቿን ድል እንደምታደርግ፤በዚያ በተቀደሰው ተራራ በኩል ለዓለሙ ሁሉ የሚያስፈልጉ ሃብታትን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ፤ ኢትዮጵያ ከ305 በላይ ጦርነት አድርጋ አንድ ጊዜ እንኳን ያልተሸነፈችበት ጥልቅ ምስጢር የታየበት፤በተለይ ስለ ኢትዮ ሐርሽ ኳርሽ የሚባል በራሪ ማሽን፤ የዓለም ሀገራት ኢትዮጵያን ይህን ያህል ዘመን የሚተናኮሉበት ዋና ምክንያትና ስለሚሰወሩ መርከቦች፤ስለ ኢትዮጵያ ታላላቅ ስውር ፍልሚያዎች፤ጸሎቶች፤መንፈሳዊ ጦርነቶችና እውናዊ ጦርነቶች ፤ በመንፈሳዊ ጦርነቶች ውስጥ ያሉ መሰረታዊ ፈተናዎችና አጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ ምስጢራዊ ሀብታት በግልጽ ያስቀምጣል፡፡