ሕይወት ምርጫ ነው

ሕይወት ምርጫ ነው

Author/s: ዮናስ አለማየሁ

Subjects

Non Fiction, Self development

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ስለ መጽሐፉ፡- ተፈጥሮ ልክ እንደ ወንዝ ሁሉ ወራጅ ነው፡፡ መልካም ሆናችሁ ክፉ ወንዙ ዝም ብሎ መፍሰሱን ይቀጥላል፡፡ ደስተኛ ሆናችኋል ወይም ተከፍታችኋል ብሎ አይጨነቅም ወይም ለእናንተ ሲል ፍሰቱንም አያቋርጥም፡፡ ወንዙ ፀጥ ብሎና ተረጋግቶ ሁሌም መፍሰሱን ይቀጥላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከወንዙ ጋር ቁልቁል ይወርዱና ደም ዕንባ ያነባሉ፡፡ ገሚሶች ደግሞ ወንዙ ወደሄደበት ቁልቁለት ቢወርዱም ቅሉ ሁሌም በሕይወት ደስተኞች ናቸው፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን ወንዙ ዝም ብሎ ከመፍሰስ በስተቀር ለምንም ለማንም ግድ የለውም፡፡ ወንዙ ለማንኛውም ሰው አድሎ ስለማያውቅ ዝም ብሎ ብቻ መፍሰሱን ይቀጥላል፡፡ ተፈጥሮም ልክ እንደ ወራጅ ወንዝ ሁሉ ፈረሰኛ ጋላቢ ነው፡፡ እየኖርን ያለንበት ተፈጥሮ እኛን በመደገፍ አብሮን ከጎናችን ይቆማል አሊያም ደግሞ በተቃራኒው ሊያጠፋን ይተጋል፡፡ ሌሎች ሕጐች በሙሉ ጸንተው የሚቆሙበት መሠረታዊው የተፈጥሮ ሕግ የመንስኤና ውጤት ሕግ [The law of Cause and Effect] ነው፡፡ የመንስኤና ውጤት ሕግ የማንኛውም ነገር ውጤት ከመንስኤው ጋር መሳ ለመሳ ነው የሚል ነው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን መንስኤው የእምነት ሥርዓት ወይም ሃሳብ ነው [The Cause is Always an Idea or Belief]. የመንስኤና ወጤት ሕግን የምንገልፅበት ሌላው መዳረሻ የመዝራትና የማጨድ ሕግ፣ ወይም የድርጊትና ግብረ መልስ [Action and Reaction] ሕግ ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ- ያለሁበትን ሁኔታ ያስከተሉብኝ ያሰብኳቸው ሃሳቦች ናቸው ማለት ነው፡፡ መልካም ምንባብ ተርጓሚ ዮናስ አለማየሁ

0.0 (0 reviews)