በትልቁ የማሰብ ኃይል

በትልቁ የማሰብ ኃይል

Author/s: ዩኒቲ መፅሐፍ መደብር ፋሲካ

Subjects

Non Fiction, Self Development

Published Year

2013 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ማንኛውም ነገር እንደማይቻል የሚነግሩህ ያልተሳካላቸው ሰዎች መሆናቸውን አስታውስ፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች አስተያየት መርዝ ነው፡፡ ስለዚህ አስተሳሰባቸው ትንሽ ከሆነና የአንተን ትልቅ ሐሳብ ለማቀጨጭ ከሚቃጡ ሰዎች ራስህን አርቅ፡፡ *** ሰዎችን ማመስገን ልመድ፡- ሰዎች ላደረጉልህ ነገር ምሰጋና ማድረግን ሕግህ አድርገው፡፡ ማንኛውንም ሰው ቢሆን የተጠቀምክበት መስሎ እንዳይሰማው ተጠንቀቅ፡፡ ምስጋናህንም በልባዊ ፈገግታ አጅበው፡፡ ፈገግታ ለሌሎች ያለህን መልካም አመለካከት ይገልጻል፡፡ «አንተ ባትኖር ምን ልንሠራ እንችል እንደነበር ግን ይገባኛል» የሚል ሙገሳንም ተጠቀም ይህ የበለጠ እንዲሠሩ ያበረታቸዋል፡፡ ስኬታማ የማይሆኑ ሰዎች እርምጃ ላለመውሰዳቸው ምክንያት ፍፁም የሚያመች ጊዜን መጠበቃቸው ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ደግሞ ፍፁም የሚያመች ጊዜን መጠበቅ ማለት ደግሞ የሰማይዋን ላም ወተት መጠበቅ ማለት ነው፡፡ ምቹ ኹኔታ የሚባል ነገር የለም፡፡ ኹኔታዎችን 'ምቹም' ሆነ 'የማይመቹ' የምናደርጋቸው እኛው ነን፡፡ *** ግብህን አስቀምጠህ ዒላማህን ለመምታት ስትጥር፣ ይህ ግብህ በውስጠ ሕሊናህ ውስጥ ይታመማል፡፡ ውስጠ ሕሊናህ ነው አዕምሮህን የሚቆጣጠረው፡፡ ለዚህ ነው በአዕምሯቸው አንድ ነገር መሥራት እንዳለባቸው እያሰቡና እየታወቃቸው ውስጠ ሕሊናቸው ባለመፍቀዱ ሰዎች በያዙት የሚሰላቹት፣ ለመወሰን የሚያመነቱት፡፡ ስለዚህ ግብህ በውስጠ ሕሊናህ ውስጥ ከታተመ ትኩረትህ በሙሉ እርሱን በማሳካት ላይ ነው የሚሆነው፡፡

4.0 (1 reviews)