አርምሞ
Summary
ማሰላሰል በቀላሉ ሲተረጎም አዕምሮን ለመቆጣጠር እና ወደበለጠ አወንታዊ እና መንፈሳዊ ሀሳቦች ብሎም ትኩረት ወደሚሹ ነገሮች ለመምራት የሚከናወን የመማርና የልምምድ ሂደት ነዉ፡፡በመሰረታዊ ትርጉሙ ማሰላሰል ማለት ሁሉንም ትኩረትህን በአንድ ነገር ላይ ማሳረፍ ማለት ነዉ ፡፡ አብዛኛዉ ሰዉ የህይወትህን ጨለማ ገጽታ ይክዳል፡፡ የወጣትነት እና የብልጽግና ፊቶችን በቢል ቦርዶቻችን እና መጽሄቶቻችንን ላይ እያሳየን አረጋዉያንንና በሞት አፋፍ ላይ ያሉትን ወደ መጦርያ ቤት እናወርዳለን ቤት አልባ ወገኖቻችንን ቸል እንላለን በድህነት ላይ የሚገኙትን አናሳ ወገኖቻችንን እና አዕምሮ ህሙማንን እና ድሆችን በየሆስፒታሉ ጥለን ያለ ረዳት እናስቀራቸዋለን ፡፡ እዉነታው ግን ህይወት ግራ የሚያጋባ የብርሃን እና ጨለማ ስኬት እና ዉድቀት የወጣትነት እና እርጅና የደስታ እና ህመም እና አዎ የህይወት እና ሞት መስተጋበር መነሃርያ ናት፡፡ሁኔታዎች ያለማቋረጥ ይለዋወጣሉ ለአንድ አፍታ ይወደወቃሉ በሚቀጥለዉ ይነሳሉ ፡፡ የዜን መምህሩ ሹንሪዬ ሱዙኪ እንዳስቀመጠዉ ሁሉም ነገር ያለማቋረጥ ‹‹በፍጹም ሚዛን ዳራ ላይ ሚዛኑን እያጣ ነዉ፡፡ የአዕምሮ ሰላምህ ቁልፍ አንተ በምትገኝበት ሁኔታ ዉስጥ ሳይሆን ለእሱ በምትሰጠዉ ምላሽ ላይ ነዉ፡፡በቡድሂስቶች እንደሚሉት የስቃይ ምንጭ ያለዉ የሌለህን በመፈለግ እና ያለህን ባለመፈለግ ላይ ነዉ፡፡ደስታ ግን ተቃራኒዉ ነዉ ባለህ ነገር መደሰት እና የሌለህን ነገር አለመራብ ነዉ ፡፡የዚህ ጽንሰ ሃሳብ ትርጉም እሴቶችህን ህልሞችህና ምኞቶችሀን መተዉ አለብህ ማለት አይደለም ነገሮችን ባሉበት ሁኔታ የመቀበል ችሎታህንና እነዚህን ማመጣጠን መቻል ማለት እንጂ፡፡ ማሰላሰል እያንዳንዱን ተሞክሮ ክፍት በሆነ አዕምሮና ከመፍረድ ነጻ በሆነ መንገድ ልብ እንድትልና ለመለወጥ ወይም ለማስወገድ ሳትሞክር እንድትቀበል ዕድል ይሰጥሃል ፡፡ ከዚያ ጉዞዉ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ ከወደቅህበት ቶሎ ለመነሳትና የአዕምሮ ሰላምህን ለመጠበቅ ማሰላሰል ሊጠቅምህ ይችላል፡፡