እየሞኽረሩ መሃየም
Summary
በ45 ርዕሶች የተቀነበበው እየሞኸረሩ መሃይምም የወግ ስብስብ መጽሐፍ ሙያውና ሙያተኛው ያሉባቸውን ህጸጾች ነቅሶ በማውጣትና መፍትሄ ለመሻት የእለት ከዕለት እንቅስቃሴዎቻችንን በገጠመኝ አዋዝቶ አቅርቦልናል፡፡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ምልከታዊ ትዝብቱን በወግ ሰንዶ ያስነበበን እየሞኸረሩ መሃየም ባህል ወግና ልማድ በእያንዳንዱ ርዕሳት ተቃኝተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሁኑ ከማለት ይልቅ ለመሆን በቅተው ትውልድ ለመቅረጽ ሀገር ለማነጽ የታተሩ ቅን አሳቢያንን አመስግኖ እንከተላቸው ዘንድ ጎትጉቶናል፡፡