የሀብት ጥበብ

የሀብት ጥበብ

Author/s: ዩኒቲ መፅሐፍ መደብር ፋሲካ

Subjects

Self development

Published Year

1937 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

Think And Grow Rich በዚህ በስኬት ሕግ ላይ የተካተቱትን አብዛኞቹን መሠረታዊ ነጥቦች ተግባራዊ በማድረግ ትልቅና ተከታታይ ተምሳሌት የሚሆኑ ታሪኮችን መፍጠር ችለናል፡፡ አጋነንክ አትበሉኝና የ Woolworth Building _ ለእነዚህ መርሆች ጤናማነት እንደማረጋገጫ የተሠራ ሐውልት ነው ሊባልም ይችላል፡፡ ኤፍ ደብልዩ ዉል ዎርዝ ይኼንን የስኬትን ሕጎችን የሚዘረዝር አዲስ ሥራህን በማንበቤ ታላቅ ክብር ይሰማኛል፡፡ ምነው ይኼን ፍልስፍና የዛሬ 50 ዓመት ባወቅኩት ኖሮ! ዛሬ የደረስኩበትን ስኬት በግማሽ ያህል ጊዜ አሳጥሬ በደረስኩበት ነበር፡፡ ዓለም ይኼንን ፍልስፍና ሲያውቅና ሲጠቀምበት ነው ያንተ እውነተኛ የሐሴት ቀን፡፡ ሮበርት ዶለር ይኼንን የስኬትን ሕጎችን የሚዘረዝር አዲስ ሥራህን ማንበብና መረዳት ማለት ከውድቀት የሚታደግ የመድን ዋስትና ፖሊሲ የመያዝ ያህል ነው፡፡ ሳሙኤል ጎምፔርስ ዕውቅ የአሜሪካ የሠራተኛ ማኅበር መሪ ያቀረብካቸው 17 ያህሉ የስኬት መሠረታዊ መመሪያዎች ጤናማ ናቸው የምለው ከ 30 ዓመታት በላይ በራሴ ቢዝነስ ውስጥ ስጠቀምባቸው ስለቆየሁና ስለማውቃቸው ነው፡፡ ጃን ዋነሜከር ነጋዴ የንጉሣዊ ቤተሰብ አባል በእነዚህ በስኬት ሕግጋቶችህ አማካይነት ለዓለም የሚሆን ትልቅ መልካም ነገር እያበረከትክ እንዳለህ አውቃለሁ፡፡ በገንዘብ ብቻ የማይለኩ ትልልቅ አሴቶችን የሚጨምር ነገር ለተማሪው የሚያጎናጽፍ በመሆኑ ለዚህ አንተ ለሰጠኸው ሥልጠና ዋጋ ቢወጣለት ምንም አይገደኝ፡፡ ጆርጅ ኢስትማን የዓለማችን ትልቁ ካሜራ አምራች እኔ ባለፉት ዓመታት ያገኘሁት ምንም ዓይነት ስኬት ቢሆን ባንተ 17ቱ የስኬት ሕጎች በመጠቀም ያገኘሁት ነው እላለሁ፡፡ ያንተ የመጀመሪያ ተማሪ በመሆኔ ትልቅ ክብር ይሰማኛል፡፡ ደብልዩ ኤም. ሪግሊይ ጄ. አር. የሀገር ዓቀፍ ደረጃ የታወቁ የቢዝነስ መሪ

5.0 (1 reviews)