የብላቴናው ማስታወሻ

የብላቴናው ማስታወሻ

Author/s: አክሊሉ ከበደ

Subjects

History

Published Year

2023-11-22

Book Type

Ebook

Summary

ስለ መጽሐፉ የደርግ መንግሥት በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሊተካ ጥቂት ወራቶች ብቻ በቀሩበት የ1983ዓ.ም ዓመት በወቅቱ በሀገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ይማሩ ነበሩ ከአስር ሺህ ያላነሱ ተማሪዎች ወደ ብላቴ የአየር ወለድ ማሠልጠኛ ለወታደራዊ ሥልጠና እንዲገቡ ተደረገ ። ተማሪዎቹ ለሁለት ወራት ያህል ወታደራዊ ሥልጠናቸውን የተከታተሉ ሲሆን ሥልጠናው ከመጠናቀቁ አስቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሀገር ጥለው ወጡ ወይም ኮበለሉ። ከዚያም በኤርትራ ሕ.ግ.ሐ.ኤ (ሻቢያ) ወያኔ (ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ) ደግሞ አዲስ አበባን በመቆጣጠሩ የደርግ መንግሥት ወደቀ። የብላቴናው ማስታወሻ በዘመቻው ተሳታፊ በነበሩ የስድስት ኪሎ የዩኒቨርስቲ ዘማች ተማሪዎች ገጠመኞችና እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመርኩዞ በልብ-ወለድ አግባብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። ታሪኩ ከልብ-ወለድነት ይልቅ እውነተኛ ታሪክነቱ እንደሚያመዝን በወቅቱ በዘመቻው ተሳታፊ የነበሩ ሁሉ በቀላሉ ሊገነዘቡት የሚችሉት ነው።

0.0 (0 reviews)