ወድቆ የተገኘው ዶክተር

ወድቆ የተገኘው ዶክተር

Author/s: አለምነህ ደሴ

Subjects

Fiction

Published Year

2006-11-11

Book Type

Ebook

Summary

የዛብና ዶ/ር ሄለን በመኪና ሆነው ከቤት እንደደረሱ የዶ/ር ባለቤት ኢንጂነር ዳዊት ከበር ቆሞ ከአንድ ጓደኛው ጋር ይጫወት ስለነበር ዶ/ር ሄለን ስትመጣ አብረው ወደቤት ገቡ፡፡ ኢንጂነር ዳዊትም “ሄልዬ አሁንኮ እናንተጋ ልመጣ ስል ነው የመጣሽው“ አለ፡፡ ሄለንም “እኔ እንኳን ጠብቄህ ነበር፤ ስታመሽ ጊዜ ያው ስራ አምሽቷል ብዬ መጣሁኝ ፡፡እነ ጋሼም ጠብቀውህ ነበር፤ በደህና ነው ዳዊት ?“ አለች “ ደህና ነኝ አንድ ፕሮጀክት ጀምረን እሱን ስንሰራ ነው ያመሸሁት፡፡ አሁንም ስለሱ ስንወያይ ነው አንቺ የመጣሽው ፡፡አዩ ምን ይሉኝ ይሆን?“ አለ፡፡ “ምን ይሉሃል የአንተ ስራ ፋታ እንደሌለው ሁሉም ያውቃሉ እንዲያውም አዩ ስላንተ ነው የምትጨነቀው ፤ስራ ይበዛበታል እያለች፡፡“ “በይ ይህ የስራ ባልደረባዬ ነው ተዋወቂው“ ብሎ አብሯት ወደ ቤት የገባውን ጓደኛውን አስተዋወቃት “ከተማ እባላለሁ“ አለ ዶክተር ብላ ሄለን ከነማዕረጓ ገለፀችለት፡፡ ኢንጂነር ዳዊት “ሄለን የምን እንግዳ ነች?“ አለ የዛብን እያየ “እነግርሃለሁ አሁን ከኢንጂነር ጋር ተጫወት “ አለች ሄለን እራት ቀርቦ እየበሉ ስለ ሥራቸው ያወራሉ፡፡ ዶ/ር ሄለን የቀረበውን አለመበላቱን አይታ “ብሉ እንጂ አልራባችሁም እንዴ“ በማለት ማቀራረብ ጀመረች፡፡ `የወንድ ሰራተኛው ውስኪ አምጥቶ ከፊታቸው አስቀመጠ፡፡ ኢንጂነር ዳዊት

5.0 (1 reviews)