ራስን ማወቅ

ራስን ማወቅ

Author/s: ዩኒቲ መፅሐፍ መደብር ፋሲካ

Subjects

Non Fiction, Self Development

Published Year

2013 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ብዙ ሰዎች ራሳቸውን ሳያውቁ ነው የሚኖሩት፡፡ ጥንካሬያቸው፤ ድክመታቸው ተስፋቸውና ህልሞቻቸው ምን እንደሆኑ አያውቁም፡፡ ይህን ይበልጥ ለማስረዳት የቻይናዎችን ምሳሌ መጥቀስ ያስፈልጋል፡፡ ቻይናውያን እንደሚሉት የሰውን መልክ የሚያሳዩ ሶስት መስታወቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ራስህን እንዴት እንደምታይ የሚያሳይ ነው፤ ሁለተኛው በሌሎች ዐይን አንተ ምን እንደምትመስል የሚያሳይ ነው፡፡ ሶስተኛው ደግሞ ትክክለኛ ገጽታህን የሚያሳይህ ነው፡፡ ስለዚህ ራስህን እወቅ፤ እውነታውን ዕወቅ፡፡ ++ ፍርሃት የአስተሳሰብ ምላሽ ነው፡፡ ፍርሃት በጊዜ ካልተወገደ ኃይልንም ያደክማል፤የፈጠራ ችሎታህን ያጠፋል፡፡ ዋናው አለመፍራት ነው፤ ዋናው የምትፈራውን በድፍረት መተግበር ነው፡፡ የፍርሃትን ምንነት በደንብ ተገንዘብ ፡፡ ፍርሃት የአንተው ፈጠራ ነው፡፡ ልክ እንደማንኛውም የፈጠራ ውጤት ማውደምና ከአንተ ማራቅ ትችላለህ፡፡ ይህም ታላቅ የራስ መተማመን ደስታ የአዕምሮ ሰላምን ያጎናፅፍሃል:: +++ በየዕለቱ ለ30 ደቂቃዎች ማንበብ በሕይወትህ ተዓምር ያስገኝልሃል፡፡ ነገር ግን ዝም ብለህ ያገኘኸውን ነገር አታንብብ፡፡ ወደ አዕምሮህ አፀድ የምትተክለው ነገር መምረጥ አለብህ፡፡ የምታነበው ነገር የመንፈስ ምግብ ሊሆን ይገባል፡፡ አንተንም ሕይወትህንም የሚለውጥ ነገር ነው ልታነብ የሚገባህ፡፡ መሳሳት ጥፋት አይደለም፡፡ ስህተት የሕይወት አንዱ አካል ከመሆኑ በላይ ለእድገት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህን ለማስረዳት አንድ አባባል ልጥቀስልህ፡፡ ‹‹ደስታ ከመልካም ፍርድ ይገኛል፤ መልካም ፍርድ ደግሞ ከተሞክሮ ይገኛል፤ ተሞክሮ ደግሞ ከመጥፎ ፍርድ ነው የሚገኘው ፡፡›› ነገር ግን ተመሳሳይ ስህተት በየእለቱ መፈጸም ጥፋት ነው፡፡ እንዲህ ያለው ነገር የሚያሳየው ራስን አለማወቅን ነው፡፡ ሰው ደግሞ ከእንስሳት የሚለየው ራሱን በማወቁ ነው::

5.0 (1 reviews)