ራስን ማሳደግ
Summary
‹‹የራስን ደረጃ ወደ ምርጥነት ለማሳደግ ተመራጭ መጽሃፍ ዶክተር ስቴፈን ኮቬይ የ‹the seven habits of highly effective people ››ደራሲ ‹‹ይህ መጽሃፍ ስለ ሁሉመ ነገር በትንሽ በትንሹ በማሳወቅ ሰዎች ምርጡን ማንነታቸዉን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ›› ዶክተር ኬኔት ብላንቻርድ የthe one minute manager ተባባሪ ደራሲ ችሎታዎችህን አሳድግ ጊዜህንና ቁሳቁሶችህን በአግባቡ ተጠቀም ፡፡አጋጣጣሚዎችን ሁሉ በመጠቀም የተመጣጠነ ግላዊና ሙያዊ ስኬትን ተጎናጸፍ ፡፡ የአዎንታዊ አመለካከት አልጋ ዎራሽ ነዉ የተባለለት የተመጣጠነ አመለካከት ህይወትህን በእጅጉ ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችልህ የአእምሮ መሳርያ ነዉ፡፡ ይህ አብዮታዊ መጽሃፍ ህይወትህን ለተራ ኑሮ አሳልፈህ መስጠት እንደሌለብህና መቼም ቢሆን የሚገባህን ምርጡን ኑሮ የምታገኝበት ችሎታና አቅም እንዳለህ ያሳይሃል ፡፡ መጽሃፉን አንብበህ ስትጨርስ ከምትማራቸዉ ነገሮች መካከል ምርጡን ጥያቄ ስለ መጠየቅና ምርጡን መልስ ስለማግኘት በማንኛዉም አጋጣሚ ገንቢ ዉሳኔን ስለማሳለፍ በእለት ተእለት እንቅስቃሴዎችህ ስለመደሰት ራስህን ጠልፈህ እንዳትጥል ስለመጠንቀቅና የአእምሮህን ሙሉ አቅም ስለመጠቀም ረባሽ ስሜቶችህን ስለመቆጣጠርና አላስፈላጊ ባህርያትን ስለማስወገድ በንግድና ግለሰባዊ ግንኙነቶችህ እጅግ ዉጤታማ ስለመሆን ሌሎች ምርጡን ማንነታቸዉን እንዲያዎጡት ስለማስቻል