የኢትዮጵያ ታሪክ
Summary
ከአራት ሚሊዮን ዓመታት በፊት፣ በኢትዮጵያ ምስራቃዊ ጠረፍ በነበረው የወሎ ግዛት አካባቢ የለመለመ መስክ እና የተንጣለለ ሐይቅ ነበር፡፡ ያ ጥንታዊ ሐይቅ ቢደርቅም ለጥንታዊ የሰው ዘር ተመራማሪዎች ታላቅ ገፀ-በረከት አስቀምጦላቸዋል እሱም ሉሲ (ድንቅነሽ) ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ማዕከል ከመሆኗም በላይ አዱሊስ የበርካታ የደንጊይ ሕንፃዎች፣ ግድቦች፣ ቤተ-መቅደሶችና የመስኖ እርሻ ማሳዎች መገኛም ነበረች፡፡በተመሳሳይም አክሱማውያኑ ከተከዜ በስተደቡብ የነበሩትን የአገው ቋንቋ ተናጋሪ ገበሬዎችን ለማስገበር እና የሰሜን ተራሮችን ለመቆጣጠር፤ ወደ ደቡብ ምስራቅ በመሔድ በእጣን ምርቱ የሚታወቀውን የአፋር በረኃን ለማስገበር፤ ቀይ ባሕርን በመሻገር ደግሞ በወቅቱ ሂጃዝ በመባል የሚታወቀውን የሳውዲ ዐረብያን ግዛት ማስገበርና የባሕር ላይ ንግዱን ከስጋት ነፃ ማድረግ ያስቻለ ወታደራዊ መስፋፋት አድርገው ነበር፡፡ የአክሱም መገበያያ ገንዘቦች ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ ኢኮኖሚ ውስጥ የላቀ ሚና እንዲኖራት ከማስቻሉም በላይ መገበያያ ገንዘቡ በፐርሺህያ፣ ሮምና በሕንዱ ኩሻናስ ግዛቶች ለግልጋሎት እስከመዋል ደርሶ ነበር፡፡ የምኒልክ ታሪክ ሲነሳ ከእየሩሳሌም ሰርቆ እንዳመጣው የሚገመተው ታቦተ ጽዮን አብሮ ይነሳል፡፡ የታቦቱን መጥፋት ዘግይቶ የተረዳው ሰሎሞን ሰው ቢልክም ምኒልክና ወጣት አጃቢዎቹ የቀይ ባሕርን ተሻግረው ነበር፡፡ በክብረነገሥት መጽሐፍ አጠቃላይ ገለፃ መሠረት ምኒልክ ከአባቱ ሰሎሞን በላይ የተመረጠ በመሆኑ እግዚአብሔር ታቦቱን አስይዞ ላከው፡፡ ከእስራኤል ቀጥሎም ወደ ተመረጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ ክርስትናን ይቀበል ዘንድ ላከው የሚልና የሰሎሞንሥርወ-መንግሥት ምስረታን ከኢትዮጵያውያን የአይሁድ ክርስትና አቀባበል ጋር በማያያዝ ያትታል፡፡ ታሪኩ ለኢትዮጵያውያን የተለየ ክብርን ከማጎናፀፉም በተጨማሪ የተመረጡ ሕዝቦች መሆናቸውን ይገልፃል፡፡ ……….አሜሪካን ኤርትራን ለተቆጣጠረው ሻዕቢያ ዕውቅና ሰጠች፡፡ የሻዕቢያ ሊቀመንበር ኢሳያስ አፈወርቂ ዋሽንግተንን ሲጎበኝ የአገሪቷ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አቀባበል አደረጉለት፡፡ የአሜሪካውያኑ አቀባበል አገሪቷ የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት አክብራ የቆየችበትን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲዋን መቀየሯን አመላከተ፡፡