የመተው ጥበብ

የመተው ጥበብ

Author/s: Dr. Tesfay Solomon Tsegay

Subjects

Self development, Non Fiction

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

የህይወት አይቀሬዎች ዉጥረትና ንዴት ዉጥረት ብሎም ንዴት የሚያመነጩት ነገሮች እኛ በምንፈልገዉ መንገድ ኢንዲሆኑ ስራዎች እኛ በምንፈልገዉ መንገድ ብቻ ኢንዲሰሩ ሰዎች እኛ እንደፈለግናቸዉ ሳይሆኑ ሲቀሩ (በአመዛኙም አይሆኑም )ዉጥረትና ንዴት ዉስጥ እንገባለን ፡፡ይሁን እንጂ እንዲህ መሆን ነበረባቸዉ የሚለዉን ሃሳብ ችላ ብለን ብንተዉና እዉነታዉን እንዳለ ብንቀበለዉና ብናደንቀዉ ኖሮ ዉጥረቱና ንዴቱ ይተዉን ነበር ፡፡ ስራን ማቆየት ስራን በይደር የምናቆየዉ እንዳይበላሽብን በመፍራት ከባድ ነዉ ብለን በማሰብ ግራ በመጋባትና ምቾት በማጣታችን ነዉ ፡፡ ከዚህ ይልቅ ነገሮች ቀላል መሳካት ያለባቸዉና ምቾት ሚሰጡ መሆን አለባቸዉ የሚሉትን ሀሳቦች ወይም ምኞቶች ብንተዉና ነገሮች በብዙ መልኩ ሊከሰቱ ወይም ሊሆኑ ይችላሉ ብለን ብንቀበል ኖሮ ስራዉን አሁኑኑ መጀመር እንችል ነበር ፡፡ ልማዶችና አደናቃፊዎች ብዙ ሰዎች ልማዶቻቸዉን ለመቀየር የሚቸገሩት ልማዱን ለማቆየት በመፈለግ ሲሆን የሚያዉቁትን መተዉ ተከትሎ የሚመጣዉ ፍርሀትም ሌላዉ ምክንያት ነዉ ፡፡አደናቃፊዎችና ሙሉ ቀን የምንፈልገዉም በተመሳሳይ ምክንያት ነዉ፡፡ በሰዎች ላይ ተስፋ መቁረጥ በሰዎች ተስፋ የምንቆርጠዉ ልክ እንደ ንዴት በምንፈልገዉ መንገድ ስለማይካሄዱ እንደምንጠብቃቸዉ ስለማይሆኑ ነዉ፡፡ ይህም ከነሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ይጎዳል ምክንያቱም በነሱ እንናደዳለን ይህ ደግሞ ደስተኞች እንዳንሆን ያደርገናል ፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን እንደምንፈልጋቸዉ መሆን አለባቸዉ ማለትን ተወት ማድረግ እነሱን ባሉበትና እንደሆኑት መቀበል ብሎም ከነሱ ጋር መሆን ይሻላል ፡፡ ይህ ግንኙነቱን የበለጠ ጥሩ ያደርገዋል፡፡ ማጣትና ሞት የምወደዉ ሰዉ ሲሞት ወይም ዉድ ንብረታቸዉን ወይም ስራችን ስናጣ ወይም በከባድ በሽታ ስንስቃይ ለከባድ ሃዘንና ስቃይ እንዳረጋለን ፡፡ ምንም ማድረግ የማይቻል ቢሆንም ወይም ማስወገድ ባንችልም ሀዘኑን እንዳለ በመቀበል ማጣቱ እንዳለ እንዲሆን መፍቀድ መቀበል ወይም ችላ ማለት ግን ሳይጠቅመን አይቀርም፡፡ ፍረሃት የችግሮቻችን ምንጭ ፍርሃት ነዉ ስራን ከማቆየት እስከ ቢዝነስ አለመጀመር እስከ የክብደት መጨመር፡፡ የፍርሃት ምንጭም ነገሮችም እንደፈለግናቸዉ እንዲሆኑ መፈለግን ወይም መጠበቅ ነዉ፡፡ነገሮች እንደምንፈልጋቸዉ እንዲሆኑ መፈለግን ችላ ብለን ስንተዉ ፈርሃትንም ላለማድረግ እንችላለን ፡፡ ችላ ብለን እንተዉ በሰላም እንኑር ግነኙነታችን እናድስ ህመምና ስቃያችንን እንፈዉስ

5.0 (1 reviews)