አገልፋኖ

አገልፋኖ

Author/s: ከፈለኝ ዘለለው

Subjects

Fiction, Literature, Philosophy

Published Year

2004 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

"አገልፋኖ" "አገልፋኖ" ከሁለት ኢትዮጵያዊ ቃላቶች ተነጥለው በወጡ ፊደላት ውህደት የተወለደ አዲስ ቃል ነው፡፡ ይኸውም "አገልግል" ከሚለው ቃል "አገል" የሚለውን ሦስት ፊደል "ፋኖስ" ከሚለው ቃል ደግሞ "ፋኖ" የሚሉትን ሁለት ፊደሎች ወስጄ በማጣመር .. "አገል" + "ፋኖ" = "አገልፋኖ" የሚለውን አዲስ ቃል ፈጠርኩ፡፡ ለዚህም አዲስ ቃል "እኛ የሰው ልጆች ወደዚህች ምድር ላይ የመጣነው እንደ "አገልግል" በውስጣችን የተቀመጠውን መልካም የሕይወት ስንቅና በጎ ሀሳብ ለሰው ልጆች ሁሉ ያለመሰሰት አውጥተን በመስጠት … እንደ ፋኖስም ሆነን የዚህች ዓለም ኑሮ ለጨለመባቸው ወገኖች ሁሉ በእኛነታችን ውስጥ ያለ ብርሃንን ያለንፍገት በመፈንጠቅ መልካምነትን በምድር ላይ ለማብዛት ነው" የሚል የግል ፍልስፍና ለበስ ትርጉምን ሰጠሁት፡፡ "አገልፋኖ" ሀገርኛ ተረትና ብሂሎቻችንን ከመልዕክት አዘል ታሪኮች ጋር በማዋደድ ፤ የለሙ ጭብጦች እጥር ምጥን ባለ የአፃፃፍ ውቅር ተደራጅተው ለክቡር አንባቢያን የቀረቡበት ሁለተኛ መፅሐፌ ነው፡፡ "አገልፋኖ" ብርታትን የሚያጋሩ አጫጭር ታሪኮችን ውስጠተ - ንቃትን ከሚያላብሱ ግጥሞች ጋር አጣምሬ ፤ የደከመ ወኔን በጥንካሬ ለመገንባት እንዲሁም ዳግመኛ ለሚወለድ አዲስ ሕይወት አዲስ ምዕራፍን የሚያመላክት ፤ በተስፋ ዕጦትም የቀዘቀዘ መንፈስን በነዳጅነት ያተጋ ዘንድ በ 2004 ዓ.ም ያሳተምኩት መፅሐፍ ነው፡፡

5.0 (1 reviews)