የዝንጀሮዎች ሠርግ !

የዝንጀሮዎች ሠርግ !

Author/s: መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን

Subjects

Non Fiction, Science

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ኢትዮጵያ እጅግ ማራኪ የሆኑና ታይተው የማይጠገቡ ድንቅዬ የተፈጥሮ ሀብቶች ጣሪካዊ ቦታዎች አሏት ፡፡ጥንታዊ አድባራትና ገዳማት ፣እንዲሁም የተለያዩ የዱር እንስሳትን አቅፈው የያዙ ደኖችና ፓርኮች ሊጠቀሱ ከሚገባቸው መሀከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው ፡፡ የውጭ አገር ጎብኝዎች ጥንታዊ አድባራትንና ገዳማትን፣ እንዲሁም የተፈጥሮ ሀብቷን ለመጎብኘት ወዳገራችን ሲጎርፉ እኛ ግን ‹‹ በጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል ! ›› እንዲሉ ሆኖ አብዛኞቻችን የተፈጥሮ ሀብቶቻችን የት እንዳሉ እንኳን በቅጡ አናውቅም ፡፡ ሌላው ቀርቶ አንድ የዋርካ ዛፍ የወይንና የዋርካ ፍሬዎችን በተለያዩ ወቅቶች እያፈራረቀ የሚያፈራ መሆኑን የምናውቅ በጣት የምንቆጠር ነን ፡፡ እንዲሁም ሰባት የወይራ ችግኞች ሕይወት ዘርተው እግር አውጥተው ፣ወንዞችን ተሻግረውና ጋራዎችን ዙረው አንድን መነኩሴ ተከትለው ሄደው ከሌላ አገር ፀደቁ የሚል ታሪክ ቢተረክልን ለማመን ቀርቶ ለመስማትም የምንቸገር ጥቂቶች አንሆንም ፡፡ ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ አንዲት ዶሮ በዕንቁላል ፈንታ የወርቅ እንክብሎችን ጥላ በዚሁ መዘዝ ባለቤቷ ለእሥር መዳረጉን ወሬ የሰማን ስንቶቻችን እንሆን ? የጭላዳ ዝንጀሮዎች ማኅበራዊ ኑሮና የጋብቻ ሥነ-ሥረዓት ከሰዎች እንደማያንስ ምን ያህሎቻችን እናውቃለን ? ዝንጀሮዎች ባለቃ እየተመሩ በሥርዓት የሚኖሩ ናቸው ፡፡ እነዚህንና ሌሎችንም ድንቅዬ የተፈጥሮ ጸጋዎች በመጎብኘትና መልሶም ለልጆች መተረክ ትልቅ ቁም ነገር አለው ብዬ ስለማምን የዚህ መጽሐፍ አዘጋጅ ከጥቂት አዛውንቶች ጋር በመሆን ባንድ ወቅት ተድባበ ማርያምን የመጎብኘት እድል አጋጥሞኝ ነበር ፡፡ ስለዚህ ባይኔ ያየኋቸውን ታሪካዊና አስደናቂ ነገሮች ሁሉ ‹የዝንጀሮዎች ሠርግ!› በሚል ርእስ ‹ጉብኝትና የወርቅ እንክብሎችን የምትጥል ዶሮ! › የተሰኙ ሦስት ታሪኮችን ያካተተች መጽሐፍ አሳትሜ ለልጆች ቁም ነገር ያላቸውን ነገሮች ለማስጨበጥ ጥረት አድርጌለሁ ፡፡ ይች መጽሐፍ ለልጆች ብቻ ሳትሆን ላንደኛ ደረጃ መምህራንም እንደ መሠረታዊ መመሪያ ልታገለግላቸው ትችላለች ፡፡ በተለይም ለሙዋእለ ህፃናት አስተማሪዎች ጠቀሜታዋ እጅግ የጎላ ነው ፡፡ግርምትን የሚፈጥሩ አዲያዲስ መረጃዎችም የተንፀባረቁባት ስለሆነ የምትሰጠው ዋጋ ከፍተኛ ነው ፡፡ በተረፈ ልጆች ተምረው ለቁም ነገር በቅተው ይችን ሳታጣ ያጣች አገር ለመጥቀም እንዲበቁ መልካሙን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ ፡፡ (ደራሲው )

0.0 (0 reviews)