አሞዛ

አሞዛ

Author/s: ከፈለኝ ዘለለው

Subjects

Non Ficition, Self Development, Philosophy, Communication

Published Year

2007 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

"አሞዛ" ወሎ ውስጥ በአንዲት መንደር የሚነገር ቤተኛ ቃል ነው፡፡ የአማርኛ መዝገበ ቃላችንም "አነባበሮ" ፣ "ወፍራም" ፣ "የሚያጠግብ እና አሸናፊ የሚያደርግ እንጀራ" የሚል ትርጓሜን ይሰጠዋል፡፡ "አሞዛ" መፅሐፍ ጥቂት ገፆቹን አንብበው በርካታ እፎይታ ሰጪ ግንዛቤዎችን ጨብጠው የሚለወጡበት ፤ በነሻጭና ለዋጭ አጫጭር ታሪኮች የተዋዙ ሕይወት ቀያሪ መልዕክቶችን የሚሸምቱበት ፤ ለዓለማዊ ኑሮም ስንቅ በሚሆኑ ግዙፍ ጭብጦችን የሚጎናፀፉበት ፤ የደከመ መንፈስን ማትጊያና ማንቂያ በ 2007 ዓ.ም ታትሞ ለንባብ የበቃ ሦስተኛ መፅሐፌ ነው፡፡ በዚህ መፅሐፌ ውስጥ በምድራዊ ችግሮች የነፈዘ አዕምሮን የሚያበረቱ እንዲሁም በውጥረጥና ጭንቀት የናወዘ መንፈስን የሚያተጉ ርዕሰ ጉዳዬች በሳቢ ስልት ተዳሰዋል፡፡ በአጫጭርና አይሰለቼ ጥበባዊ አቀራረቦች የሰው ልጅን የአስተሳሰብ ጉድፋት የሚያነፁ ቅን ምልከታዎች ከቀያሪ ታሪኮች ጋር ተቀምረው ቀርበውበታል፡፡ በተጨማሪም ድንበርና ወሰን የማይገድባቸው የሀሳብ ዳሰሳና ቅኝት በጥልቀት ይታዩበታል፡፡ ውስጣችንም አስተውሎና ልብ ብሎ የማያውቃቸውን እንግዳ ጉዳዬች በጎላ አስተማሪነት ያስነብባል፡፡

0.0 (0 reviews)