
ከአመጿ ጀርባ
Summary
"ከአመጿ ጀርባ" በሁለት መቶ አስራ አራት ገጾችን፣ እና ሰባት ምዕራፎችን የያዘች የረጅም የልቦለድ መጽሀፍ ነች። መጽሀፏ፡ ስነልቦናዊ፤ ግለሰባዊ ብልጽግና (self-development)፣ መንፈሳዊ ሂደቶችን እና እራስን ፍለጋን ይዳስሳል። መጽሀፉ የተለያዩ ጠጣር ማህበራዊ ሀሳቦችን ያነሳል፣ይሞግታል። ሰውነትን ዋጋ፣ የእውነትን ትልቅነት፣ የእይታን መጥበብ፣ መስፋትና ንቃትን በህይወት መንገድ ላይ ቆሞ ያመላክታል። "ከአመጿ ጀርባ" አንዲት የአይምሮ ሀኪም ጋር እየተመላለሰች የህይወቷን ውጣ ውረድ የምታጋራ አመጸኛ ሴት ታሪክ ላይ ያጠነጥናል።