ደጓ እናት

ደጓ እናት

Author/s: ዝጋለ አያሌው

Subjects

Sociology, Spiritual, Religion, Non Fiction

Published Year

2014 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

ሙሉ በሙሉ መንፈሳዊና ታሪካዊ፤በአለንበት ዘመን ያሉ/የተፈጠሩ የሚታዩ ታምራቶች፤በተለይ በማትታየዋ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ መንፈሳዊ በረከቶች፤ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለዓለሙ እንደሚያስፈልጉ፤ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ በርካታ ገዳማት ከሶሪያና ከግብጽ በንሥር ተጭነው ወደ ኢትዮጵያ እየመጡና እየተጠራቀሙ መሆኑን፤ እዲሁም አንዳንድ ሰዎች፤በተለይ ከክርስትና ውጭ ያሉ ሰዎች ስለጸበልና ስለ ጥምቀት ክርስትናን ያጣጣሉ መስሏቸው‹‹ እናንተ ክርስቲያኖች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ውኃ ንፁሕ የውኃ ቧንቧን እየተረጫችሁ ፀበል ትላላችሁ ›› በማለት ይሳለቃሉ፡፡ ንጹሕ ውኃ በመረጨት መቀደስ እንደሚቻል ኮ! መጽሐፍ ቅዱስ አስቀምጦልናል፡፡ እነሆ ማስረጃ፡- ‹‹ጥሩ ውኃንም እረጫችኋለሁ፤ እናንተም ከእርኩሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ከጣዖታችሁ ሁሉ አነጻችኋለሁ፤አዲስ ልብንም እሰጣቸኋለሁ፤አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ፡፡ ት፤ሕ 36፡25-26›› ይላል፡፡ ስለዚህ ጥሩ ውኃንም ማለት ንጹሕ ጥሩ የሆነ ውኃን ማለት አይደል? ብቻ በዚህ ጉዳይ ወደ ውስጥ ቢዘለቅ አውሎ ያሳድራል፡፡ አባቶቻችን ጸበልን፤ቦታንና ቤተ መቅደሶችን በፈጣሪ ስም አከበሩት፡፡ ቅዱሳኑ ለፈጣሪ ያከበሩትን ነገር እስቲ ማን ይሽራል?›› በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለደራሲው ከአእምሮ በላይ የሆኑ ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ አንደኛ ድንጋይ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሆኖ ረዥም መንገድ ያስጓዘበትን ገዳም ማየትና፤ ጸበል ገብቶ ሲጠመቅ በቀስተ ደመና የተከበበባቸውን ቦታዎች ማየቱና በዚህ በዓለንበት ዘመን 48 ከባድ የጦር መሳሪያ አንድን ገዳም ለማጥፋት ተተኩሶ አንዱ እንኳን ጥቃት ሳያደርስ፤48ኛው ግን ተመልሶ የጦር መሳሪያ የወረወሩ ሰዎችን ደምስሷቸዋል፡፡ የአጥፍቶ ጠፊዎችን መቃብር በአካል መጎብኘት ነው፡፡ ብቻ በተጉለት ምድር ገና ያልተነገረና ያልታየ ታምርና ታሪክ አለ፡፡ ብቻ በተጉለት ምድር ከገባን ጴንጤም፤ሙስሊምም፤ክርስቲያንም ቄዳር ሲጠመቅ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ደጓ እናት! መንፈሳዊና ሥጋዊ ፈተናዎች ያሰቃዩት ሰው ይሕን መጽሐፍ ፈጥኖ ያንብብ፡፡

0.0 (0 reviews)