ደብተራ

ደብተራ

Author/s: ቃለጽድቅ በላይነህ

Subjects

Poetry, Literature

Published Year

2012 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

"ደብተራ" ከትርጉሙ ጀምሮ በውስጡ እስከያዘው ሐሳብ ተገርሜያለሁ፡፡ የግጥም ጉልበቱ ያስደምመኛል፡፡ በ "ብተራ" ሥብሥብ ግጥሞች እያንዳንዳቸው ብቻ ለብቻ ሥብከት ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ጸጋ(ሥጦታ) የተለያየ ነውና "ቃለጽድቅ" መክሊት ይሔ ይመስለኛል፡፡ ዓውደ ምሕረት ላይ ከሚሠብከው ሰባኪ (በአቻነት) ግጥሞቹ ሚዛን ይደፋሉ፡፡ ለብዙዎቻችን አስተማሪ፣ መካሪ፣ አስታዋሽ ንቁ ዓይነት ሐሳብ ጫሪ ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመንፈስም በሥጋም ሀብታም መሆኗን "ቃለጽድቅ" በሚገባ አሳይቶናል፡፡ የቃላት ምርጫው የአተራረክ መንገዱ ድንቅ ነው፡፡ ብናነበው ለሥጋም ለነፍስም እናተርፍበታለን፡፡ አርቲስት ዋሲሁን በላይ ጥበብ ማደሪያዋን አሳምራ ታውቃለች ምክንያቱም ጥበብ ስለሆነች፡፡ አንዳንዱን በልጅነቱ ሌላውን በውርዝውናው፣በጎልማሳነቱ አብዛኛውን በዕርግናው ዕድሜ፤ ታዲያ ቃለጽድቅን በውርዝውና ዕድሜው ላይ ወጥራ ይዛዋለች፡፡ ከምህንድስና ሙያው ልታፋታው ይመስላል፤ ቀናተኛ ስለሆነች ደባል አትፈልግማ! በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ዲግሪ ያለው በተጨማሪም በማሪን ኢንጂነሪንግ (መርከበኝነት) የተመረቀ ድንቅ ወጣት ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለጥፋቸው ወቅታዊ ግጥሞች ቀልብ የሚስቡ ልዩ ተሰጥዖ እንዳለው ሹክ የሚሉ በመሆናቸው እድምተኛ ከሆንኩ ሰነባብቻለሁ፡፡ የመጀመሪያ የግጥም ልጁን እነሆ ብሎናል የወደፊቱ ባለ ቅኔ ለመሆኑ አልጠራጠርም፡፡ መልካም ንባብ ብያለሁ፡፡ ኢንጂነር ጌዴዎን ደጀኔ

0.0 (0 reviews)