ዛጎል

ዛጎል

Author/s: እንዳለጌታ ከበደ

Subjects

Fiction, Literature

Published Year

ኅዳር 2013 ዓ.ም፡፡

Book Type

Ebook

Summary

‹ዛጎል› (ለመጀመሪያ ጊዜ፡- ጥቅምት 1998 ዓ.ም የወጣ) በኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ እምብዛም ትኩረት ባልተሰጣቸውና በተለምዶ ‹ቡዳ› ተብለው በሚጠሩና መገለል ስለሚደርስባቸው ማኅበረሰቦች አካላዊና ኅሊናዊ ጉዳት ላይ ያጠነጠነ ረጅም ልቦለድ ነው፡፡ በተጨማሪም ‹ዛጎል› ደብራ ሰምራ ተብላ በምትጠራ የደራሲው ምናብ በፈጠራት ከተማ ውስጥ የተፈጠረውን ርሃብ ለጊዜው ለማስወገድ በማሰብ፣ የክርስቶስ ሰምራን ታቦት ሽጠው ገንዘቡን ለማኅበረሰቡ በማዋላቸው፣ ይህ ድርጊታቸው ደግሞ ከቀናት በኋላ በመታወቁ ሕይወታቸው ስለተመሳቀለባቸው ወጣት መምህራን የሚተርክ ነው፡፡ ልዑልሰገድ ጌታቸው የተባሉ አንድ የከፍተኛ ትምሕርት ተቋም የሥነ ጽሑፍ ተመራማሪ፣ ‹‹ዛጎል››ን አስመልክተው በሠሩት አንድ ጥናት ውስጥ፣ ‹‹ደራሲው እንዳለጌታ በሳላቸው ገጸባህርያት አማካኝነት የዘመኑን ትውልድ አኗኗር፣ ትውልዱ ከማኅበረሰቡ ጋር የሚያደርገውን ግጭትና ችግርን ለመፍታት አይደፈሬ የሆኑትን የሚደፍር መሆኑን አሳይቶናል›› ብለዋል፡፡

5.0 (1 reviews)