የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ ከጥንት እስከ ዛሬ

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ ከጥንት እስከ ዛሬ

Author/s: አክሊሉ ከበደ

Subjects

History, Non-Fiction

Published Year

2014 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

"የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ከጥንት እስከ ዛሬ" በሚል በደራሲ አክሊሉ ከበደ ኢረና (አምባሳደር) የቀረበው ይህ መጽሐፍ የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ታሪክ ከቅድመ-አክሱም ዘመን አንስቶ እስካለንበት የለውጥ ዘመን (የብልጽግና መንግሥት) መባቻ ድረስ ያለውን ታሪክ በስፋት ያስቃኛል። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በዓለማችን ላይ በጥንታዊነት የምትታወቅ ቀደምት ሀገር እንደመሆኗ፣ ረጅም ዘመናትን ተሻግሮ እዚህ በደረሰው ታሪኳ ውስጥ እንደ ሕዝብና መንግሥት ከሌሎች ሀገራት ሕዝብና መንግሥት ጋር የነበራትን የፖለቲካ፣ የጸጥታ፣ የኢኮኖሚ፣ የባህል፣ የሃይማኖታዊ፣ የቴክኖሎጂ ግንኙነቶች በሰፊው ይዳስል። በመጽሐፉ በየዘመኑ የነበሩ የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶችን ብቻ ሳይሆን ያጋጠሟትን ተግዳሮቶች፣ በተለያዩ ዘመናት ኢትዮጵያን የመሩ ነገሥታትና መሪዎች የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስከበር የሄዱባቸውን መንገዶች፣ የመሪዎቿ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶቻችውንና ውድቀቶቻቸውን፣ በሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ከተለያዩ አካላት የተሰነዘሩ ጥቃቶችና የሀገሪቱ መሪዎች ጥቃቱን የመከቱበትን ዘዴዎችን በርዕስ በርዕስ ይተነትናል። በመጽሐፉ ከተነሱ አንኳር ጉዳዮች መካከል ስለ የውጭ ፖሊሲ፣ ስለ ሀገራዊ ሕልውናና ሉዓላዊነት፣ ስለ ባህር በር፣ ስለ ድንበር ጉዳዮች፣ ስለ ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ስለብፓን አፍሪካኒዝም፣ ስለ ሁለትዮሽ ግንኙነቶች፣ ስለ ተባበሩት መንግሥታት፣ ስለ ዓለምአቀፍ ንግድና ንግድና ኢንቨስትመንት፣ ስለ ገጽታ ግንባታ፣ ስለ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ፣ ስለ ባህል ልውውጥ፣ ስለ ዳያስፖራ ዲፕሎማሲ ይገኙበታል። መጽሐፉ መሰል ቀደምት ሥራዎች ባልነበሩበት ወቅት ደራሲው ካላቸው የግል ንባብ፣ ምርምርና የሥራ ተሞክሮ በመነሳት ፈር ቀዳጅ የሆነውን ይህን ጠቃሚ በመጽሐፍ ሰንደው ማቅረባቸው የሚያስመሰግናቸው ሲሆን አንባቢም ከመጽሐፉ ብዙ እውቀትን ሊገበይበት ሊያተርፍበት እንሚችል እሙን ነው።

0.0 (0 reviews)