ሕይወት እንዲህ ናት
Summary
...ምስጋናችን የሚጀምረው ሃሌ ሉያ ብሎ ነው። በመጀመሪያው ፊደላችን የሚጀምረው ሃይማኖት ከማኅፀን ሳለን ጀምሮ በተአምራዊ አካሄድ ያስኬደን መንገድ ነው። ነብዩ ዳዊት "ከናቴ ማኅፀን ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ" ማለቱ ከማኅፀን ሲሠራ ጀምሮ ኑሯችን በሃይማኖት ስለሆነ ነው። በሃይማኖት ከሚያዩት ሀገራቸው ከሚያውቋቸው ዘመዶቻቸው ተለይተው ወደ ማያዩት አባት እግዚአብሔር ወደ ማያውቁት ሀገር መንግሥተ ሰማያት የገቡ ብዙዎች ናቸው። አቡነ አረጋዊ ከነዚህ አንዱ ናቸው። ኢትዮጵያን በሃይማኖት እንጅ በትውልድ አያውቋትም። ኢትዮጵያዊያንም አባ አረጋዊን በሃይማኖት እንጅ በሥጋ አይዛመዷቸውም። አየኸው: በሃይማኖት ስትኖር ባልተወለድህበት ስፍራ ትኖራለህ። በሃይማኖት በማያውቁህ ሰዎች መካከል ትከበራለህ። በሃይማኖት ስትኖር እንኳን አፈሩን ሰማዩን ያንተ ታደርጋለህ። በባዕድ ሀገር ስትኖር አትፈራም። ቋንቋውን ባማትሰማው ሕዝብ መካከል ሰሚ አታጣም። በሃይማኖት የሌላውን ትወስዳለህ፣ያንተንም ትሰጣለህ...