አርምሞ

አርምሞ

Author/s: ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ

Subjects

Fiction, Self development, Literature

Published Year

2014 ዓ.ም.

Book Type

Ebook

Summary

አርምሞ ጥናታዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ፣ መንፈሳዊ፣ ጥበባዊ ረጅም የፍቅር ልቦለድ ሲሆን በግለ-ምህንድስና (Self-Engineering) ላይ ያተኮረ ድርሳን ነው። አርምሞ ውጫዊውን ውጥንቅጥ በውስጣዊ ጉዞ እንድንገታው አበክሮ በጥበባዊ ቃላት፣ በወካይ ገፀ ባህሪያት ይተርክልናል። በ250 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ12 ምዕራፋት ተሸንሽኖ፣ መስከረም 2014 ዓም ታትሞ ለንባብ የበቃው አርምሞ በአንባቢዎች ዘንድ በጣም ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን በአራት ወራት ብቻ 6 ጊዜ በተደጋጋሚ ታትሟል። ብዙዎችም ምስክርነታቸውን የሠጡት ሥራ ነው። ለምሳሌ(ዶ/ር መ/ቢ ሮዳስ ታደሰ ስለ አርምሞ መጽሐፍ) በአንድሮሜዳ የቴሌቭዥን መርሐ ግብር ላይ በመቅረብ ሰፊ ኢትዮጵያዊ ዕውቀትን ያጋራን ዶ/ር ኤልያስ አርምሞ በሚል ዐዲስ የምርምር፣ የፍቅር፣ የሃይማኖት ይዘት ባለው የልብ ወለድ መጽሐፍ ብቅ ብሏል። ፈላስፋውም "ተናግሮ ብሩር ውእቱ አርምሞሰ ወርቅ ይእቲ" (መናገር ብር ነው። ዝምታ ግን ወርቅ ናት) ይላል። ከሚጮህ ሳንቲም ዝምተኛው ብር ዋጋው ይልቃል። ድምፅ የሚያሰማ፣ የሚንቦጫቦጭ ትንሽ የውሃ መጠን የያዘ ያልሞላ እንስራ ሲኾን፤ ድምፅ የማያሰማው እንስራ በአግባቡ የውሃ መጠን ይዞ የሞላው ነው። በሥጋ፣ በነፍስ፣ በመንፈስ የተዋቀረው የሰው ልጅ የውስጥ ውስጥ የኾነው መንፈሱ ታላቅ የምስጢር ቋት እንደኾነ፤ ከአእምሮ ጠባይ ይልቅ አእምሮ መንፈሳዊው መዝገበ ምስጢር እንደኾነ ኹሉ ውስጡ በአርምሞ የታከመ ውጪውም ጤናማ ነው። ውሳጣዊ ልቡ የተረጋጋ ከልቡ መዝገበ ቃላትን ወልዶ ቢናገር እንኳ አንደበቱ እንደ እሳት ወላፈን አይፋጅም፣ የሰው ዐጥንት በስድብ ቃል አይሰብርም። ይልቁኑ ፈዋሽ፣ ጠጋኝ፣ የሚያረጋጋ ይኾናል እንጂ። በባሕር ውስጥ ማዕበል የተነሣባት ጀልባ ለመኼድ እንድትቸገር ውስጡ የታወከበትም፣ አርምሞን ያልያዘ በእግረ ኅሊና ለመኼድ፣ እደ ኅሊናውን ለመዘርጋት፣ በዕዝነ ልቡና ለመስማት፣ በአብራከ ልቡና ለማንበርከክ ያዳግተዋል። በአጠቃላይ ተመስጧዊ ሕይወት የራቀውና አእምሮ መንፈሳዊን ገንዘብ ማድረግ ያዳግተዋል። በመኾኑም አርምሞ መጽሐፍ ማንበብ ለስክነት በእጅጉ ይጠቅማል።

0.0 (0 reviews)