ቀልበ ሙሉ ህይወት
Summary
ቀልበ ሙሉ መሆን በእያንዳንዷ የህይወታችን ቅጽበት የሚያስፈልገን ጥበብ ነዉ፡፡በተለይ ደግሞ አሁን ባለንበት ወቅት ሃሳቦቻችንና ስሜቶቻችንን ከቁጥጥር ዉጭ እየወጡ ለአለመግባባትና ግጭት እየዳረጉን መተሳሰብና መተባበር ርቆን እርስ በርስ እየተናቆርን ባለንበት ወቅት ረጋ ማለት ሰብሰብ ማለት መቻል በጣም ወሳኝ ነዉ፡፡ ለመሆኑ ሀሳብ /ማሰብ /ከየትስ ነዉ የሚመጣዉ መቆጣጠር ይቻል ይሆን ከተቻለስ እንዴት ስሜቶቻችንስ ከየት ነዉ የሚመነጩት መግራትስ እንችላለን ወይ ከቻልን እንዴት መሪዎቻቸን ህዝባቸዉን ልብ ብለዉ ያደምጣሉ ወይ ሲወስኑ በሙሉ ቀልባቸዉ ነዉ ወይስ በጥድፍያና በዉጥረት ዉስጥ ሆነዉ ነዉ ሰራተኞች በስራቸዉ ደስተኞች ናቸዉ ወይ ከስራ ይረቃሉ ጤናቸዉን ደህንነታቸዉ ካልተጠበቀ ለሚሰሩላቸዉ ተቋማት አመርቂ ዉጤት ያስገኛሉ ወይ መምህራንና ተማሪዎች በሙሉ ቀልብ ነዉ ወይ የሚያስተምሩትና የሚማሩት ስፖርተኞች በልምምድና በዉድድር ወቅት ከሚሰሩት ጋር በሚገባ እየፈሰሱ /ፍሎው እያደረጉ/ ነዉ ወይስ ስለሚመጣዉ ዉድድር እየተጨናነቁና እየተጠበቡ ነዉ የጤና ባለሙያዎች (ከሃኪም እስከ ጽዳት ሰራተኛ )ስራቸዉን በሚገባ ትኩረትና ልብ ማለት እየሰሩ ነዉ ወይ ራሳቸዉንስ በሚገባ እየጠበቁ ነዉ ወይ እያገለገሉ ያሉት ፡፡ በአጠቃላይ ከግል እስከ ተቋም ብሎም እስከ ሃገር ቀልበ ሙሉ ዜጎችና መሪዎች ያስፈልጉናል ላለፉት አርባ አመታት ብዙ ግለሰቦች ቢዝነሶች ተቋማትና መንግስታት ቀልበ ሙሉነትን በተግባር ስለዋሉ በብዙ ምልኩ ተጠቃሚ እንደሆነ ጥናቶች አረጋግጠዋል ፡፡እኛም እንደ ግለሰብና እንደ ሀገር በዚህ እድሜ ጠገብ ልምምድ ተጠቃሚ እንሆናለን የሚል ጽኑ እምነት አለኝ ፡፡