ሀገር በቀል የሥራ አመራር ጥበብ

ሀገር በቀል የሥራ አመራር ጥበብ

Author/s: ኃይሉ መኮንን

Subjects

Management, Self Development

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ሥነ ቃል የአንድ የዳበረ ቋንቋ የእድገት መገለጫ ነዉ፡፡ ሥነ ቃል አንድን ሃሳብ መልእክት፤ እዉቀት እና ጥበብ ከተራ ቃላቶች፤ ሃረጎች፤እና ዐረፍተ ነገሮች በበለጠ የሚገልጽ የሚያብራራ የሚያሰተላልፍ የሚያስታውቅ እና የሚያስረግጥ የቋንቋ አንዱ ዘርፍ ነዉ፡፡ ስነ ቃል ራሱን የቻለ የቋንቋ ጥበብ ነዉ፡፡ ስነ ቃል በዉስጡ የተለያዩ የስነ ቃል አይነቶች አሉት፡፡ በዚህ መጽሃፍ ላይ ለጥቅም የዋለዉ ምሳሌያዊ አነጋገር ወይም ዘይቤያዊ አነጋገር የተባለዉ የስነ ቃል ዘርፍ ከሚያሥተላልፋቸዉ ዋና ዋና ጥበቦች መካከል አንዱ የስራ አመራር ጥበብን ነዉ ፡፡ የኢትዮጵያ አገር በቀል የስራ አመራር ጥበብ በአማርኛ ቋንቋ ዉስጥ ሆኖ አገልግሎት ሲሰጥ የኖረ የቋንቋ ሀብት ነዉ፡፡ነገር ግን ይሄን አገር በቀል የሥራ አመራር ጥበብ ከቋንቋ ጥበቡ ተነጥሎ ባለመቀመጡ ወይም ባለ መያዙ እንዲሁም ባለመዳበሩ እና ባለ መደራጀቱ የተነሳ ከሥራ አመራር ጥበቡ መገኘት የነበረበት ጥቅም በበቂ ሁኔታ አልተገኘም ፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ በአማርኛ ቋንቋ ሥነ ቃል ዉስጥ በምሳሌያዊ አነጋግር ተካቶ የኖረዉን አገር በቀል የሥራ አመራር ጥበብ ከቋንቋዉ ስነቃል ለይቶ አዉጥቶ በማጥናት እና በማደራጀት ከዘመናዊዉ አመራር የአመራር ጥበብ /Moderen Management Types/ጋር አነጻጽሮ በማቅረብ ጥበቡን በተለየ መልክ ራሱን የቻለ የኢትዮጵያ አገር በቀል የሥራ አመራር ጥበብ እንደሆነ ለተጠቃሚዉ ማስተዋወቅና ለአጠቃቀም ምቹ ማድረግ ነዉ ፡፡ ኃይሉ መኮንን

0.0 (0 reviews)