ከወደቀው ዋርካ

ከወደቀው ዋርካ

Author/s: ዮሐንስ ሞላ

Subjects

Biography

Published Year

2017 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ክላሽ የታጠቀን ወታደር ‘የመሸበት የእግዜር እንግዳ’ ብሎ ቤቱ ወስዶ እንደማሳደር ካለ ደግነት አንስቶ፣ ድንገት ‘ግልፍ’ ያደረገውን ፖሊስ በጥፊ እስከ መምታት የደረሰ ቁርጥ ኃይለኝነት... በእነዚህ ጠርዝ እና ጠርዞች መሀል ያሉ ትውስታዎች የተቋጠሩበት የአባት ማስታወሻ ነው። አባት ሞላ ናማጋ በ99 ዓመታት የዚህ ዓለም ቆይታው፥ በአመነበት መንገድ ላይ — ወዲህ፥ ‘ኀይለኛ’ ባስባለው ጽኑ አቋሙ፣ ወዲያ፥ 'ሩኅሩህ' ባሰኘው ደግነቱ መሀል፣ የልቡን እውነት እንደ ልቡ ኖሮት አልፏል። በአመነበት መልኩ ኖሮ '...ከእንግዲህ ዕድሜ አልለምንም። የፈለግኹት ሁሉ ሆኖልኛል...' ካስባለው ሕይወቱ መሀል፥ አድረው ትዝታ፣ ከርመው ማስታወሻ የሚሆኑ አሥራ አራት ታሪኮች በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ተካተዋል። መልካም ንባብ።

4.0 (4 reviews)